Song Lyrics

ከመገኘትህ ወዴት እሄዳለሁ

Apostle Yohannes Girma
Amilake Destaye
ከአፈር የተነቀለ ሳር ጠውልጐ ደርቆ እንደሚታይ ልምላሜን ርቆ ከሕልውናህ ውጭ መኖር ለእኔ ይከብዳል ክፍት ክፍት እያለ ሁሌ ሆድ ያስብሳል (2x) አዝ፦ ከመገኘትህ ወዴት እሄዳለሁ ከህልውናህስ ምንን እመርጣለሁ ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን (2x) በእጆችህ አጥብቀህ እኔን ይዘኸኛል ይህንንም እውነት ቃልህ ይናገራል ነገሩ ከገባኝ ዕንቁ መሆንህ ለምን አንተ ብቻ እኔም ልያዝህ/ላጥብቅህ (2x) አዝ፦ ከመገኘትህ ወዴት እሄዳለሁ ከህልውናህስ ምንን እመርጣለሁ ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን (2x) ከአንተ እርቆ ሰው እንዴት እንደሚኖር እኔ አይገባኝም ትምክህቱ ምን ይሆን ከህልውናህ ውጭ እልፍ ከሚያጅበኝ ከመገኘትህ ውስጥ የተጣልኩ ያድርገኝ (2x) አዝ፦ ከመገኘትህ ወዴት እሄዳለሁ ከህልውናህስ ምንን እመርጣለሁ ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን ሳበኝ አስጠጋኝ ከጉያህ ሥር ዙሪያው ብርድ ነው ፈለኩ ሙቀትህን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection