የመውደዴን ብዛት የፍቅሬንም ብዛት በውስጤ ያለውን የንዳዱን ብርታት የማረከኝን የተረታሁልህን ልገልጠው አልችልም አንተ ያረከኝ (2x) አሸንፈኸኛል እመሰክራለሁ ጌታ አፌን ሞልቼ እናገራልሁ (2x) የአንተ ፍቅር ውስጤ ያለው እየጨመረ የሚሄድ ወንዝ ነው አሁንስ አየሁ ይህ ገብቶኛል አልወጣው ነገር ይዞኛል (3x) የምልህ አለኝ የምልህ ቋንቋን አጥቼ አኖርኩልህ ቃላት አግኝቼ መጥቻለሁ ኢየሱስዬ ወድሃለሁ (2x) ኧረ ማን ሊተካህ አንተን (2x) ስፍራህን የሚወስድ ከወዴት ሊገኝ በሰማይ የለም በምድርም የለም ከምድርም በታች አይገኝ (2x)