አቅም ስጠኝና አብዝቼ ልውደድህ መቼም ልጥገብህ አልል አንተ አትጠገብም ሰው ቢያንገራግር እስከሚገባው ነው የበራለት ለታ ለመውጣት የሚያስቸግር ፍቅርህ እጅግ ብርቱ ነው አዝ፦ ከጠዋት አንስቶ እስከሚመሽ ድረስ ከምሽት አንስቶ እስከ ንጋት ድረስ ብትወደድ አትጠገብም (3x) የእኔ ጌታ እወድሀለሁ (3x) ጌታ እወድሀለሁ (3x) ጌታ ኢየሱስ ላልወድህ አልችልም ላልቀርብህ አብዝቼ የተገኘሁብህ አንተ እኮ ነህ ምንጬ እጅግ ጥልቅ ነው ያለን ትስስር ከጥንት የነበረ ዛሬም ያለ ለዘለአለም የሚቀጥል ነገር አዝ፦ ከጠዋት አንስቶ እስከሚመሽ ድረስ ከምሽት አንስቶ እስከ ንጋት ድረስ ብትወደድ አትጠገብም (3x) የእኔ ጌታ እወድሀለሁ (3x) ጌታ እወድሀለሁ (3x) ጌታ ኢየሱሴ ከጥንት ከማለዳ የኔ ያንተ ነገር ማቆምያም የለውም ጊዜያትን ሲሻገር ሁሉ ነገር ያልፋል አንድ ሳይቀር ጠፊ ነው ለኔ ያለህ ነገር እኔም ላንተ ያለኝ ነገር ዘለዓለም ኗሪ ነው አዝ፦ ከጠዋት አንስቶ እስከሚመሽ ድረስ ከምሽት አንስቶ እስከ ንጋት ድረስ ብትወደድ አትጠገብም (3x) የእኔ ጌታ እወድሀለሁ (3x) ጌታ እወድሀለሁ (3x) ጌታ ኢየሱስ