የምድር ዳርቻዎች ፈጣሪ ውሆችን በእፍኝህ የሰፈርህ ሰማየ ሰማያት የአንተ ናቸው በግርማዊነትህ ሰራሃቸው ጥንት የነበርህ ዛሬም ያለህ ለዘለአለም የምትኖር (2x) አዝ፦ አንተ ዘለአለም ነህ (2x) ጅማሬና ፍጻሜ የሌለህ ጌታ አልፋና ኦሜጋ (2x) ሰማይና ምድር በስፍራቸው ሳይኖሩ አንተ ነህ ቀድመሃቸው ጅማሬ የለህም ፍጻሜ እድሜህ አይሰላ ሰው አይደለህ ጥንት የነበርህ ዛሬም ያለህ ለዘለአለም የምትኖር (2x) አዝ፦ አንተ ዘለአለም ነህ (2x) ጅማሬና ፍጻሜ የሌለህ ጌታ አልፋና ኦሜጋ (2x) ከአማልክት መሃከል እንደአንተ ማን ነው የእኔን ጌታ እግዚኣብሔር የሚመስለው አምላኬ ከሁሉም ትለያለህ አንተ የአማልክት ሁሉ አምላክ ነህ ጥንት የነበርህ ዛሬም ያለህ ለዘለአለም የምትኖር (2x) አዝ፦ አንተ ዘለአለም ነህ (2x) ጅማሬና ፍጻሜ የሌለህ ጌታ አልፋና ኦሜጋ (4x)