አቅም ስጠኝና አብዝቼ ልውደድህ መቼም ልጥግብህ አልል አንተ አትጠገብም ሰው ቢያንገራግር እስከሚገባው ነው የበራለት ለታ ለወጣት የሚያስቸግር ፡ ፍቅርህ እጂግ ብርቱ ነው ከጥዋት አንስቶ እስከሚመሽ ድረስ ከምሽት አንስቶ እስከንጋት ድረስ ብትወደር አትጠገብም (፫x) የእኔ ጌታ እወድሃለሁ(፫x) ጌታ እወድሃለሁ(፫x) ኢየሱስ ላልወድህ አልችልም ላልቀርብህ አብዝቼ የተገኘሁብህ አንተ እኮ ነህ ምንጬ እጅግ ጥልቅ ነው ያለን ትስስር ከጥንት የነበረ ዛሬም ያለ ለዘላለም የሚቀጥል ነገር ከጥዋት አንስቶ እስከሚመሽ ድረስ ከምሽት አንስቶ እስከንጋት ድረስ ብትወደር አትጠገብም(፫x) ኢየሱሴ እወድሃለሁ(፫x) ጌታ እወድሃለሁ(፫x) ኢየሱስ ከጥንት ከማለዳ የእኔ የአንተ ነገር ማቆሚያ የለውም ጊዜአቱን ሲሻገር ሁሉ ነገር ያልፋል አንድ ሳይቀር ጠፊ ነው ለእኔ ያለህ ነገር እኔም ለአንተ ያለኝ ነገር ዘላለም ኗሪ ነው የእኔ ጌታ ከጥዋት አንስቶ እስከሚመሽ ድረስ ከምሽት አንስቶ እስከንጋት ድረስ ብትወደር አትጠገብም(፫x) ኢየሱሴ እወድሃለሁ(፫x) ጌታ እወድሃለሁ(፫x) ጌታ ኢየሱስ