ደስ የሚልህን ስጦታ በእጄ ያለኝን ጌታ ራሴን ላድርግ መስዕዋትህ ከሁሉ በላይ የምሰጥህ ኑሮህን ጨርሰህ በእኔ ኑር ካሰብከው የሚቀርህ አይኑር ( 2x) በአንተ መኖር ያሰብከውን መኖር ኑሮህን መኖር መርጫለሁ ብኖር ለአንተ ብሞትም ለአንተ ከፈቃድህ ስር ይሁን መቃብሬ ከዚህ ሌላ ኑሮ/ሕይወት አይታየኝም እኔ ( 2x) በላይ ያለው ፈቅድህ በምድር በእኔ እንዲሆን ይኸው ራሴን አምጥቻለሁ ለአንተ እንዲሆን ሰጥቻለሁ ለክብርህ መገለጫ ዕቃ የወደድከውን ማድረጊያ ( 2x) እንደ ወትሮው በሥጋዬ ከብሮ ሳየው ውድ ጌታዬ ልጁን በእኔ መልክ ገልጦት ያሰበውም ሰምሮለት ደስታዬ ያን ጊዜ ይሞላል መሻቴ ፍጻሜን ያገኛል ( 2x) በአንተ መኖር ያሰብከው መኖር ኑሮህን መኖር መርጫለሁ ብኖር ለአንተ ብሞትም ለአንተ ከፈቃድህ ስር ይሁን መቃብሬ ከዚህ ሌላ ኑሮ/ሕይወት አይታየኝም እኔ ( 2x)