Song Lyrics

የልቤ ደስታ

አዝ፦ የልቤ ደስታ ጌታ የልቤ ደስታ የሱስ በገናዬን ልያዝ ልቀኝልህ ነፍሴ ውላ ታድራለች በስምህ (2x) ምንም በሌለበት ማይነጥፍ ደስታ ብር ያልደጋገፈው የዚህ አለም ስጦታ ፊትን የሚያበራ ከላይ የሆነው ዘላቂው ደስታዬ ጌታ ባንተ እኮ ነው አዝ፦ የልቤ ደስታ ጌታ የልቤ ደስታ የሱስ በገናዬን ልያዝ ልቀኝልህ ነፍሴ ውላ ታድራለች በስምህ (2x) አይኖቼን ወደ ተራሮች ባነሳ መመኪያን ለማግኘት ለእኔ የሚሳሳ ለአይን የሚሞላ ከቶ አንድም አላየሁ ይልቅ ባንተ ሆነ ልቤን ደስ የሚለው አዝ፦ የልቤ ደስታ ጌታ የልቤ ደስታ የሱስ በገናዬን ልያዝ ልቀኝልህ ነፍሴ ውላ ታድራለች በስምህ (2x) በስደት ምድር ላይ በደረቅ በረሃ ለአይን ተስፋ ሳይኖር ለጥም የሚሆን ውሃ ዙሪያ ሲጨላልም መጽናናት ሲሳነኝ በእንግድነት ሀገር ስራህ መዝሙር ሆነኝ አዝ፦ የልቤ ደስታ ጌታ የልቤ ደስታ የሱስ በገናዬን ልያዝ ልቀኝልህ ነፍሴ ውላ ታድራለች በስምህ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection