Song Lyrics

ስትወድ ብዙ

ስትወድ ብዙ ስትምር ብዙ ደግነትህ አበዛዙ መልካምነትህን ለእኔ አልቆጠብከው ለያንዳንዱ ነገር አብዝተህ አየሁ ከለመንኩህ እና ካሰብኩት በላይ ሁሉ ተከናውኖ ተደርጎልኝ ሳይ ምለውን አጣሁ ዝም አሰኘኝ የአንት ስራ አስደነቀኝ (2x) አዝ፦ ከተደረግልኝ በጎነት አንዳችም ለእኔ ማይገባ ነበር እንደ ቸርነትህ አርገሃልና እደነቃለሁ አብዝቼ ተመስገን እላለሁ (2x) ኃይሌ እንዳልል አይደል ብዙ ብልጠት በዝቶ አልደርስኩ ለእኔ አንተ በርትተህ ተናጥቀህልኛል በርትተህ ተውግተህ ምርኮን በዝብዘሃል እንካ ምሥጋናዬን ላንት ላብዛ ላብዛ ሳልጠግብ ውዳሴህም አፌን ከቶ አልዝጋ ወዳጄ ነህ የምወድህ ከሁሉ በላይ የማበልጥህ (2x) አዝ፦ ከተደረግልኝ በጎነት አንዳችም ለእኔ ማይገባ ነበር እንደ ቸርነትህ አርገሃልና እደነቃለሁ አብዝቼ ተመስገን እላለሁ (2x) ሙት ነበርሁ የማረባ ከምንደሬ ስትገባ ምን ነበረኝና ምኔን ወዶ ልበል የትኛው እኔነቴ ለዚ ሳበው ልበል እንዲያው ቸርነትህ ያ ፍቅርህ ካልሆነ አይገባኝም መድሃኒቴ የእኔ ጌታ የአንተ ውለታ (2x) አዝ፦ ከተደረግልኝ በጎነት አንዳችም ለእኔ ማይገባ ነበር እንደ ቸርነትህ አርገሃልና እደነቃለሁ አብዝቼ ተመስገን እላለሁ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection