አነባ ጌታዬ አፈር ላይ ተደፍቶ የወደቀበትን ጭንቀት ተመልክቶ ጌታዬ ተጨንቆ አባዬ ሆይ አለ አጋዥ አልተገኘም ለጌታ የዋለ መስቀል ተሸክሞ ትከሻው ተጣለ ግርፋቱ በዛ ግርፋቱ ተመለጠ ራቁቱን ደም ሲያፈስ በቀራንዮ ዋል አንገቱ ደፋ ሲል ዕዳ ተከፈለ አዝ፦ ጌታዬን አከብራለሁ (3x) በኑሮዬ ጌታዬን አከብራለሁ (3x) በኑሮዬ ዝናን ከበሬታን ሞገስን በሥጋ ሊያገኝ ወዶ ነፍሱን ከዓለም ከሚያስጠጋ ይሻላል ጭጋፉ ውዳቄን መሳይ በሥጋው ተንቆ በእምነት ጌታን የሚያይ አዝ፦ ጌታዬን አከብራለሁ (3x) በኑሮዬ ጌታዬን አከብራለሁ (3x) በኑሮዬ ማቆ በመከራ ጐስቋላ አካል ይዞ በረሃን የሚዘልቅ ጌታን ተመርኩዞ ተሸማቆ ኑሮውን ለጌላ ሲል ችሎ ያለፈን አየሁት አክሊል ተቀብሎ አዝ፦ ጌታዬን አከብራለሁ (3x) በኑሮዬ ጌታዬን አከብራለሁ (3x) በኑሮዬ በሞቱ እኔን መስሎ ጌታን ተከትሎ ወድቆም የሚነሳ አልሸነፍ ብሎ ለጠላቱ ታግሎ የማታ የማታ ጌታው ምሎለታል እርሱ እንደሚረታ አዝ፦ ጌታዬን አከብራለሁ (3x) በኑሮዬ ጌታዬን አከብራለሁ (3x) በኑሮዬ ጌታዬን አከብራለሁ (3x) በኑሮዬ ጌታዬን አከብራለሁ (3x) በኑሮዬ