Song Lyrics

አንዴ ቆርጠናል

Addisu Worku
Ande Kortenal
ሰልፉ ተከማቸ ጦር ተወረወረ የወንጌሉን ዘማች ያዙልኝ ተባለ የሞት ጥላ ረዝሞ ለሰሚው ቢያስፈራም መጋደልን ለምደናል ለአምላካችን ስራ አዝ:- አንዴ ቆርጠናል ተከትለናል በእምነት ጀምረን በድል እናከትማለን (2x) ስጋው ለመከራ ቁርበቱን ለአለንጋ አማኝ የሚያቀርበው ላመነበት ዋጋ እንደዚህ ከሆነ አምላክ ይሁን ያለው እንኳንስ መከራ ይሁን የፈቀደው አዝ:- አንዴ ቆርጠናል ተከትለናል በእምነት ጀምረን በድል እናከትማለን (2x) የመድህኑን ተስፋ ባይገነዘቡ ስለ ሽልማቱ መዋረድ ኮከቡ አምላክ ባይኖርለት ተረስቶ ነበር ትላንት የታደገው ዛሬም በእርግጥ አለ አዝ:- አንዴ ቆርጠናል ተከትለናል በእምነት ጀምረን በድል እናከትማለን (2x) በስጋችን ፈርደን በነፍስ ቆርጠናል የደህንነት ጉዞ አንዴ ጀምረናል ወድቀንም ተነስተን ይህን ሁሉ ስናልፍ በድል እንዘጋለን የሕይወትን ምዕራፍ አዝ:- አንዴ ቆርጠናል ተከትለናል በእምነት ጀምረን በድል እናከትማለን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection