Song Lyrics

ድሉን አውጃለሁ

Addisu Worku
Ande Kortenal
የሕይወቴንም እራፍ አቅጣጫ የለወጠ ድንጋይ ልብ ወስዶ ስጋ ልብ የሰጠ ድቅድቅ ጨለማ ሕይወቴን ያበራ የእርሱን ውለታ ዳግም ዳግም ላውራ አዝ:- ኮረብታ ላይ ቆሜ ድሉን አውጃለሁ የመንግስቱን ግርማ ክብር አወራለሁ ዛሬም ኢየሱስ ያድናል ዛሬም ያክንዱ ይሰራል የድል ወንጌል ይሄው በአለም ይነገራል የመከራ ውሃ እየተጐነጨ ላቡን በከንቱ ለበረሃ የረጨ ዛሬ ታድሶ ወዙ ተመልሷል መቅደሱ ገብቶ አምላኩን ያነግሳል አዝ:- ኮረብታ ላይ ቆሜ ድሉን አውጃለሁ የመንግስቱን ግርማ ክብር አወራለሁ ዛሬም ኢየሱስ ያድናል ዛሬም ያክንዱ ይሰራል የድል ወንጌል ይሄው በአለም ይነገራል ጉልምስናዬ ወንጌል አገልግሎ ሕይወቴ አላማው በአንተ ተጠቃሎ አንተን አንግሼ አንተን የማይበት ይሁን ሕይወቴ ጌታ ንገሥበት አዝ:- ኮረብታ ላይ ቆሜ ድሉን አውጃለሁ የመንግስቱን ግርማ ክብሩን አወራለሁ ዛሬም ኢየሱስ ያድናል ዛሬም ያክንዱ ይሰራል የድል ወንጌል ይሄው በአለም ይነገራል ዛሬም ጌታዬ ነፃነት ይሰጣል ከዙፋኑ ፊት በረከት ይወጣል ስሙን ላነግሥ በፊቱ ቆሜያለሁ ሕይወቴን በድል እፈጽማታለሁ አዝ:- ኮረብታ ላይ ቆሜ ድሉን አውጃለሁ የመንግስቱን ግርማ ክብሩን አወራለሁ ዛሬም ኢየሱስ ያድናል ዛሬም ያክንዱ ይሰራል የድል ወንጌል ይሄው በአለም ይነገራል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection