አምላኬን ልባርክ አፌን እከፍታለሁ ለወደደኝ ጌታ ምስጋናን እሰዋለሁ ተመስገን እላለሁ በመከራ ጊዜ ፈጥኖ ደርሶልኛል ነፍሴ ትገዛለት ፍቅሩ አሸንፎኛል (2x) ለመድህኔ ይሁን ምስጋና ድሃ አደጉን አስቧልና የሚያረካ ፈጸሞ በአለም እንደ ኢየሱስ የለም አዝ:- ሰማይ ዙፋኑ መቀመጫው ምድርም ለእግሮቹ መረገጫ ስሙ ምን ጊዜም የሚረታ ትላንትም ዛሬም ነገም ጌታ የእኔ መድህን ጌታ ብርቱ መታጠቂያው ድንገት ሲላላበት የጦረኛው መውጊያው ጦር ሲሰበርበት (2x) ተከላካይ ጋሻው ከእጁ ሲወድቅበት መከታ ነው ያለው ተገኔ ነው ያለው ምሽግ ሲናድበት መድህኔ ግን ሁሌ ባለ ድል ድል አድራጊ ክንዱ የማይዝል ታላቅ አምላክ የኔ መከታ ሁሌ የሚረታ አዝ:- ሰማይ ዙፋኑ መቀመጫው ምድርም ለእግሮቹ መረገጫ ስሙ ምንጊዜም የሚረታ ትላንትም ዛሬም ነገም ጌታ የእኔ መድህን ጌታ ሆ እየተባለ ተስፋ የተጣለበት በጊዜው የሰው ልጅ የተጋደለበት የተራረደበት ዛሬ ተረት ሆኖ በትዝብት ይወራል የኢየሱስ ነገር ግን እያደር ያብባል እያደር ይጥማል የ እግዚአብሔር ልጅ ሁሌ አሸናፊ የጠላቱን ድፍረት ገፋፊ በዙፋን ላይ ሁሌ የሚኖረው ኢየሱስ ጌታ ነው አዝ:- ሰማይ ዙፋኑ መቀመጫው ምድርም ለእግሮቹ መረገጫ ስሙ ምንጊዜም የሚረታ ትላንትም ዛሬም ነገም ጌታ የእኔ መድህን ጌታ (2x)