አዝ:- እኔ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁኝ ያለው የደሙ ፍሬ ነኝ (2x) እኔም እንደሌላው አለሁኝ ነበርኩኝ ብዬ ምናገረው ከበደሌ ሌላ ምንም ነገር የለኝ የምዘረዝረው ሰው መስሎት ቢክበኝ ሁሉን እንደከንቱ ቆጥሬ እተዋለሁ ይልቁን በሞቱ ጌታን እንድመስለው ለዚያ እዘረጋለሁ አዝ:- እኔ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁኝ ያለው የደሙ ፍሬ ነኝ እኔስ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ ምህረት የተቀበልኩ ሞት የተሻረልኝ እድለኛ ሰው ነኝ ከመቃብር ወዲህ ቀሪ የሆነውን ታሪክ ከምሰራ ጊዜ የሚሽረውን ነገ የሚረሳውን ዝና ከማወራ ዘላለማዊውን ሕይወት የሆነውን ላውዛ ያንን ዜና የእግዚአብሔር አብ ፍቅር የጌታችን ታሪክ እርሱ ይበልጣልና አዝ:- እኔ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁኝ ያለው የደሙ ፍሬ ነኝ እኔስ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ ምህረት የተቀበልኩ ሞት የተሻረልኝ እድለኛ ሰው ነኝ ከአምላክ ጥሪ ሰምተው ለአምላካቸው ወንጌል ሌት ቀን የሚለፉ በዚያ በማይጠፋው በሕይወት መጽሃፍ ላይ ተግተው የሚጽፉ በበጉ ዙፋን ፊት በጻድቃን ማህበር ስማቸው ሲጠራ በነፍስ ተወራርደው ድል እንዳደረጉ በአንክሮ ሲወራ አዝ:- እኔ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁኝ ያለው የደሙ ፍሬ ነኝ እኔስ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ ምህረት የተቀበልኩ ሞት የተሻረልኝ እድለኛ ሰው ነኝ ጥላዋ እስክታልፍ ጀንበር እስክትጠልቅ በአምላኬ ታግዤ በሚሰጠኝ ጸጋ የጸድቅን ጐዳና እስከጫፍ ተጉዤ ቃል እንደገባልኝ ለእረፍት ሲጠራኝ አክሊል ቢጠብቀኝ ከሁሉም የሚበልጥ የነፍሴ መድኃኒት ፊት ነው የሚናፍቀኝ አዝ:- እኔ በበኩሌ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ በመስቀል ላይ ሆኖ ተጠማሁኝ ያለው የደሙ ፍሬ ነኝ እኔን ብትጠይቁኝ የኔ ነው የምለው ምንም ታሪክ የለኝ ምህረት የተቀበልኩ ሞት የተሻረልኝ እድለኛ ሰው ነኝ