Song Lyrics

ማን እንደ እግዚአብሔ

Addisu Worku
Ande Kortenal
ዘንዶውን የወጋህ እባቡን የረገጥክ ባህሩን ሰንጥቀህ ህዝብህን ያሻገርክ በክብር ያረገህ በክብር የምትመጣ አንተ አይደለህም ወይ ነፃ የምታወጣ አንተ አይደለህም ወይ አዝ:- ማነው ማነው እንደ እግዚአብሔር ያለ ታዳጊዬ ለሚታመኑበት ተዋጊ የገሃነምን ዘር ገርስሷል ከሳሼ አፍሮ ተመልሷል (2x) የእነ ሲድራቅ አምላክ የዳንኤል ታዳጊ ከእቶን የምታድን የአምበሳን አፍ ዘጊ በዘመናት ሁል ኡከህዝብህ ጋር የቆምክ በከሳሻቸው ፊት ልጆችህን ያስከበርክ አንተ አይደለህም ወይ አዝ:- ማነው ማነው እንደ እግዚአብሔር ያለ ታዳጊዬ ለሚታመኑበት ተዋጊ የገሃነምን ዘር ገርስሷል ከሳሼ አፍሮ ተመልሷል (2x) ሃያላን በግርማ ፈጥነው ሲሟሽሹ በአክብሮት በፍርሃት ከፊቱ ሲሸሹ መራፉን ይዘጋል ፍጥረት በቀጠሮ ጌታ ብቻ ይኖራል ዘላለም ተከብሮ( አዝ:- ማነው ማነው እንደ እግዚአብሔር ያለ ታዳጊዬ ለሚታመኑበት ተዋጊ የገሃነምን ዘር ገርስሷል ከሳሼ አፍሮ ተመልሷል (2x) ይሄ ታላቅ አምላክ እኛን ከመረጠን በጸጋው ሸፍኖ ህዝቤን አጅብ ካለኝ አንተ ብቻ አምላክ ሁንልን ብለናል ታቦቶቻችንም በእግርህ ስር ጥለናል ለአንተ ተማርከናል አዝ:- ማነው ማነው እንደ እግዚአብሔር ያለ ታዳጊዬ ለሚታመኑበት ተዋጊ የገሃነምን ዘር ገርስሷል ከሳሼ አፍሮ ተመልሷል (2x) ጠላቴ አፍሮ ተመልሷል ከሳሼ አፍሮ ተመልሷል(3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection