Song Lyrics

በአለንጋ አልገታኝም

Addisu Worku
Ande Kortenal
በአለንጋ አልገታኝም የበረት ዘንግ ይዞ አላስማረከኝም ሰይፉን በኔ መዝዞ (2x) ከዚህ በሚበልጥ ኃይል በፍቅሩ ጎበኘኝ ጉልበቴን አስገዛ መስቀሉን ሊያሳየኝ (2x) አዝ:- ሃሌ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (3x) መስቀልህ አወጀው ነፃነቴን ቃልህም አጸናው መሠረቴን መከራ ስቧጥጥ ጉዞ ሲከብድብኝ ተንሸራትቼ እንድወድቅ ከስር ሲናድብኝ (2x) የድል ቀን ቢነጋ ኢየሱስ ሞተና በጠላት ተጫማሁ ኃይል አገኘሁና (2x) አዝ:- ሃሌ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (3x) መስቀልህ አወጀው ነፃነቴን ቃልህም አጸናው መሠረቴን ከጐንህ ፈስሶልኝ ፍቅርህን ጠጥቻለሁ ከተበሳው እጅህ ሆዴን ሞልቻለሁ (2x) የእግሮችህ ቀዳዶች ያጫሙኝ ጠላት ላይ የራስህ ላይ እሾህ ሆነኝ ክብርህን እንዳይ (2x) አዝ:- ሃሌ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (3x) መስቀልህ አወጀው ነፃነቴን ቃልህም አጸናው መሠረቴን ኑሮዬ ይገባሃል አንተ ሚስጥረኛዬ የነፍሴ ፍላጎት ይሄ ነው ጌታዬ (2x) ጠላት አደናግጦ ልክድህ ሲያባብለኝ ያንተን ጣራ አስቤ እንድመለስ እርዳኝ (2x) አዝ:- ሃሌ ሃሌሉያ ሃሌሉያ (3x) መስቀልህ አወጀው ነፃነቴን ቃልህም አጸናው መሠረቴን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection