Song Lyrics

ከሞትም ያድናል

Addisu Worku
Yemeskelu Fikir
በሞት ጥላ የሚያድር በግዞች ሸለቆ ጠላት የሚመታው አሸምቆ ከአንበሳው መንጋጋ ለጣር የተጣለ ነበር ወገኔ የቆሰለ አዝ፦ ከሞትም ያድነዋል ከሞትም ያድናል ከሞትም ያድናል ኢየሱስ (2x) ጌታ ደርሶለታል ወንጌል ልኮለታል ሰማያዊው ብርሃን በርቶለታል መልዕክተኞች ወጡ ተላትን ገጠሙ በመስቀሉ ጉልበት ድል አደረጉት አዝ፦ ከሞትም ያድነዋል ከሞትም ያድናል ከሞትም ያድናል ኢየሱስ (2x) ዓለምና ትርፏን ወደ ኋላ ገፍቶ ከመታወቅ ይልቅ መናቅ መርጦ ዘሩን ተሸክሞ በለቅሶ የሚዘራ በደስታ ያጭዳል ከአምላክ ጋራ አዝ፦ ከሞትም ያድነዋል ከሞትም ያድናል ከሞትም ያድናል ኢየሱስ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection