ኑሮ ከጌታ ጋር ጥሞኛል ከምለየው ሞት ይሻለኛል ይወደኛል እወደዋለሁ ሚስጢሬን አካፍለዋለሁ ወዶኝ ቀርቧል ወደ ልቤ ነፍሴን አጥግቧል ተርቤ ሌላ ጌታ አያሻኝም እንደእርሱ አይሆንልኝም አዝ፦ ስሙ ይክበር የእኔ ጌታ የእኔ የግሌ መከታ ከመከራ ያወጣኛል እጁን ልኮ ያድነኛል ስሙ ይክበር (2x) ወንድም ጋሻዬ እርሱ ነው ታማኝ ጓዴ ኢየሱስ ነው በመከራ ያጸናኛል በደስታው ይሞላኛል ልቤን በፍቅሩ ያከታል ጠላቴን ይቀጠቅጣል እስከሞቴ አልተወውም ስሙን ጠርቼ አልጠግብም አዝ፦ ስሙ ይክበር የእኔ ጌታ የእኔ የግሌ መከታ ከመከራ ያወጣኛል እጁን ልኮ ያድነኛል ስሙ ይክበር (2x) ሳለቅስ እምባዬን ያብሳል ከወላጅ እናት ይብሳል ለዘለዓለም አይለይም ስሙን ጠርቼ አልጠግብም የድሆች አባት እርሱ ነው ጉስቁልናን የቀመሰው መሪአችን ነው አለቃችን እናክብረው አባታችን አዝ፦ ስሙ ይክበር የእኔ ጌታ የእኔ የግሌ መከታ ከመከራ ያወጣኛል እጁን ልኮ ያድነኛል ስሙ ይክበር (2x) ስሙ ይክበር (3x)