Song Lyrics

ኢየሱስ

Addisu Worku
Yemeskelu Fikir
ኑሮ ያለጌታ ታቅቶኝ ኀጢአቴ አስመርሮኝ ወደ ኢየሱሴ ብመለስ የእርሱ ደግነት ማርኮኝ በድል ጐዳና ብገባ ፍቅሩ ነፍሴን ብትፈታ ጉልበቴን ለጠላት ላልሰጥ ቃል ገባሁኝ ለጌታ በመከራና በጭንቀት እሮሮ ጌታን አመልከዋለሁ ኑሮ ያለእርሱ ጉዳት ነው ከእርሱ ጋር ግን ደስታ የመልካም ሁሉ መሰረት ይመስገን የእኛ ጌታ ስንጨነቅ የሚራራ ስንደክም ደጋፊያችን በበረሃ ዓለም እያለን ስንጠማ እርካታችን ዞሮ ምግቢያችን ኢየሱስ ማረፊያችን አንተ ነህ ብንከዳህ አያዋጣንም የድሃ ጐጇችን ነህ ጌታ ጌታችን ጌታችን አስታውሰን ብለን ተጣርተን ሳናፍር እስካሁን ተጉዘናል በነገር ሁሉ መጽናትን ከጌታ ተምረናል የሚያሳፍር ስም አይደለም የሰጠኸን ጌታችን ክርስቲያን ጀግንነት እንደው ይረዳል ነን ልባችን ክፉውን ሁሉ ተቃውመን ከኀጢአት ጋራ ታግለን ጉዟችን በድል ያከትማል የጌታን መስቀል ይዘን ክብር ክብር ሃሌሉያ (2x) የነፍሳት ሁሉ ምሥጋና ዙፋንህን ይክበበው በቸርነትህ ተገርሟል በልጅህ የዋጀኸው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection