Song Lyrics

ጌታ ኢየሱስ ትዝ አልከኝ

Addisu Worku
Yemeskelu Fikir
ስደክም እያደገፈ ስወድቅ አንስቶ ከእኔ ጋራ ተርቦ ስጠማ ተጠምቶ በስስታ እያየኝ ልጄ በርታ ሚለኝ ያ መልካሙ ጌታ ኢየሱስ በጣሙ ናፈቀኝ አዝ፦ ጌታ ኢየሱስ ትዝ አልከኝ ያደረክልኝ ውለታ ከዳሁህ ተታልዬ ትቀበለኝ እንደው ወደ አንተ ልምጣ ሌሎቹም ክርስቲያኖች ሄዱ በጣም ተጉ በሕይወታቸው ግለው ወደ ድል ተጠጉ ለዓለም አገልጋይ ሆኜ እኔ ግን ቀረኹኝ ያችን ኢየሩሳሌምን ከሩቅ እያየሁኝ አዝ፦ ጌታ ኢየሱስ ትዝ አልከኝ ያደረክልኝ ውለታ ከዳሁህ ተታልዬ ትቀበለኝ እንደው ወደ አንተ ልምጣ ሰላምህ ከእኔ ሸሽቶ ጭንቀቴ እየገነነ ያመንኩት ሁሉ ከዳኝ የያዝኩት ተነነ ነፍሴ እንደተጐዳች ወዜም እንዳበረ ጌታዬን ባገኘው ኖሮ እነግረው ነበረ ብዬ ገና ስናገር ናልኝ ልጄ ሲል ሰማሁት በእግሩ ስር ተደፍቼ ቅዱስ ጌታዬን ወየሁ ማረኝ አልኩት ያለፈው ትምህርት ሆኖኝ የዓለም ጉስቁልና ጉልበቴን ላላስገዛ ለዓለም እንደገና ቃል ገባሁኝ በእርሱ ፊት ዳግም ላልለየው የእኔን ጉስቁልና ለአየ መቀጣጫ ይሁነው ለአንተ እገዛለሁኝ አንተ ነህ የነፍሴ ጌታ ብቸገር ብጐሳቆል እድሌ አንተ ነህ ያለኸኝ አለኝታ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection