Song Lyrics

ምሥጋና ምሥጋና

Addisu Worku
Yemeskelu Fikir
አዝ፦ ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (2x) መከራ እንደሚያልፍ የጊዜውም ሃዘን እንደምንራመድ ሁሉን ነገር አልፈን ለቅሶ በዝማሬ ሃዘን በደስታ እንደሚለወጡ ተናግሯል ያ ጌታ አዝ፦ ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (2x) እንደበደላችን አልተከፈለንም ጌታ በመዓቱ አልተናኘንም ምህረትን የሚወድ የሰራዊት ጌታ እንዳዬን ለመክፈል በውርደት ተመታ አዝ፦ ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (2x) በኑሮዬ ሁሉ አንተን አስከብሬ በመከራ ልለፍ ከአንተ ጋር አብሬ የሕይወት እስትንፋስ ሰጥተኸኛልና መስዋዕቴ ይኸው ከነፍሴ ምሥጋና አዝ፦ ምሥጋና ምሥጋና ለኢየሱስ ምሥጋና ይገባሃል አምላክ ለአንተ ለሆንከው ገናና (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection