በሞት ጥላ የሚያድር በግዞች ሸለቆ ጠላት የሚመታው አሸምቆ ከአንበሳው መንጋጋ ለጣር የተጣለ ነበር ወገኔ የቆሰለ አዝ፦ ከሞትም ያድነዋል ከሞትም ያድናል ከሞትም ያድናል ኢየሱስ (2x) ጌታ ደርሶለታል ወንጌል ልኮለታል ሰማያዊው ብርሃን በርቶለታል መልዕክተኞች ወጡ ጠላትን ገጠሙ በመስቀሉ ጉልበት ድል አደረጉት አዝ፦ ከሞትም ያድነዋል ከሞትም ያድናል ከሞትም ያድናል ኢየሱስ (2x) ዓለምና ትርፏን ወደ ኋላ ገፍቶ ከመታወቅ ይልቅ መናቅ መርጦ ዘሩን ተሸክሞ በለቅሶ የሚዘራ በደስታ ያጭዳል ከአምላክ ጋራ አዝ፦ ከሞትም ያድነዋል ከሞትም ያድናል ከሞትም ያድናል ኢየሱስ (4x)