Song Lyrics

ምን ደላው ለእርሱ

Addisu Worku
Yemeskelu Fikir
ልደቱ በረት ሞቱ በመከራ እንጨት ላይ ዕድሜውን ፈጅቶ በስቃይ ለማልጠቅመው ለእኔ ጌታ እራሱን ጐዳ ፍርድ ተሸክሞ ወደ ሞት ተነዳ አዝ፦ ምን ደላው ለእርሱ ምን ደስ አሰኘው የመስቀል ላይ ጣሩ እንደምን ማቀቀው አዬ ፍቅር ሆኖ ሞተ እንደተገፋ የእሾህ አክሊል ጭኖ አለ አንገቱ ደፋ (2x) ፍቅርን ለብሶ ርህራሄ አስገድዶት የነፍሴ ለቅሶ ተሰምቶት መጣ የእኔ ጌታ ሞተ ተጐሳቁሎ የአባቱን ፍቃድ ፈጽሞታል ታግሎ አዝ፦ ምን ደላው ለእርሱ ምን ደስ አሰኘው የመስቀል ላይ ጣሩ እንደምን ማቀቀው አዬ ፍቅር ሆኖ ሞተ እንደተገፋ የእሾህ አክሊል ጭኖ አለ አንገቱ ደፋ (2x) ምን ዋልኩለት ለእዚህ ወዳጅ ከቶ ለሞተው እኔን ተክቶ አልተገራም ልቤ አልታረቀም ገና መቼም ተስፋ አልቆርጥ ቀን ይመጣልና አዝ፦ ምን ደላው ለእርሱ ምን ደስ አሰኘው የመስቀል ላይ ጣሩ እንደምን ማቀቀው አዬ ፍቅር ሆኖ ሞተ እንደተገፋ የእሾህ አክሊል ጭኖ አለ አንገቱ ደፋ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection