Song Lyrics

ትዝ ይለኛል

Addisu Worku
Yemeskelu Fikir
ትውስ ሲለኝ የጌታዬን ፍቅር ያደረገልኝ በጐልጐታ ከአገር ወደ አገር በመንከራተት ፀሐይና ውርጭ ሲፋረቁበት ይሁዳ ሸጦት ጴጥሮስ ሲክደው ተከታዮቹም ጥለውት ሲሸሹ የፊጥኝ ታስሮ ለፍርድ ሲነዳ ጥፊ እና ግርፉ ሲወርድበት አዝ፦ ትዝ ይለኛል ያ መድህኔ በእንጨት ላይ የሞተው ስለእኔ ትውስ ይለኛል የመስቀል ፍቅሩ ያደረገልኝ ውለታው ሁሉ አልራሩለትም አስረው ሲገርፉት ያን መልከመልካም እሩፍሩሁን ፈጠሪ የማይችለውን መስቀል አሲዘው መድህናቸውን ለፍርድ ሲወስዱ ሲጮህ ሲያነባ በጣር ተከቦ በደም ላብ ባሕር ሆኖ ሲያነባ ሲወድቅ ሲነሳ አባ አባ ሲል ተሰቃየልኝ ነፍሱ እስክትዝል አዝ፦ ትዝ ይለኛል ያ መድህኔ በእንጨት ላይ የሞተው ስለእኔ ትውስ ይለኛል የመስቀል ፍቅሩ ያደረገልኝ ውለታው ሁሉ ይረሳኛል ወይ ያ የጣር ጊዜው መድሃኒቴን እየተሳለቁበት ከመስቀል ውረድ ራስህን አድን እያሉ ጠላቶች ሲያሾፉበት ጨለማ ውጦን የነበርነውን እኛን ለማዳን ከክብሩ ወርዶ የዓለምን ኀጢአት ያስወገደውን ታላቁን መድህን ነፍሴ አትረሳውም አዝ፦ ትዝ ይለኛል ያ መድህኔ በእንጨት ላይ የሞተው ስለእኔ ትውስ ይለኛል የመስቀል ፍቅሩ ያደረገልኝ ውለታው ሁሉ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection