Song Lyrics

ጌታዬን አከብራለሁ

Addisu Worku
Ande Kortenal
አነባ ጌታዬ አፈር ላይ ተደፍቶ የወደቀበትን ጭንቀት ተመልክቶ ጌታዬ ተጨንቆ አባዬ ሆይ አለ አጋዥ አልተገኘም ለጌታ የዋለ መስቀል ተሸክሞ ትከሻው ተላጠ ግርፋቱ በዛ ገላው ተመለጠ ራቁቱን ደም ሲያፈስ በቀራንዮ ዋለ አንገቱ ደፋ ሲል እዳ ተከፈለ አዝ:- ጌታዬን አከብራለሁ (3x) በኑሮዬ (2x) ዝናን ከበሬታን ሞገስን በሥጋ ሊያገኝ ወዶ ነፍሱን ከአለም ከሚያስጠጋ ይሻላል ጭንጋፉ ውዳቂ እኔን መሳይ በስጋው ተንቆ በእምነት ጌታን የሚያይ( ጌታዬን አከብራለሁ (3x) በኑሮዬ (2x) ማቅቆ በመከራ ጐስቋላ አካል ይዞ በረሃን የሚዘልቅ ጌታን ተመርኩዞ ተሽማቆ ኑሮን ለጌታ ሲል ችሎ ያለፈን አየሁት አክሊል ተቀብሎ አዝ:- ጌታዬን አከብራለሁ (3x) በኑሮዬ (2x) በሞቱ ሊመስለው ጌታን ተከትሎ ወድቆም የሚነሳ አልሸነፍ ብሎ ለጠላቱ ታግሎ የማታ የማታ ጌታው ምሎለታል እርሱ እንደሚረታ አዝ:- ጌታዬን አከብራለሁ (3x) በኑሮዬ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection