Song Lyrics

ፍቅርን አስቀድማት

Addisu Worku
Ande Kortenal
ሌት ከቀን ደክሜ ስምህን ለማስከበር ብዙ ተጉዣለሁ ወንጌልን ለማብሰር አምላኬ እንዲህ ይላል እያልኩኝ ተግቼ ድምጼ እስከሚሰልል ነፍሳት ተጣርቼ አንዳንዴ ጉዳትን አንዳንዴም ማጣትን ስለ ስሙ ችዬ በለቅሶ ያለፍኩትን ሁሉንም ዘርዝሬ ታሪኬን ስገታ አምላኬ እንዲህ አለኝ በረቂቅ ዝግታ አዝ:- ልጄ ሆይ አድምጠኝ ስራህን አውቃለሁ ምን እንደጐደለህ እኔ እነግርሃለሁ ነፍሴን ደስ ልታሰኝ ከሆነ የአንተ ጥማት ቀዳሚ ትዕዛዜን ፍቅሬን አስቀድማት ነፍስን የሚጠግን የሚጣፍጥ ዜና ሕዝብህን የሚያንጽ ለነፍስ የሚስማማ የጠለቀ ሚስጢር ቅኔ እንደባለቅን የዜማውን ስንኝ በንጹህ አርቅቄ ለብዙ ዘመናት በቤትህ ዘመርኩኝ ሕዝብህ እልል እስኪል ስምህን አስከበርኩኝ ብዬ ብዘረዝር ያማላሁኝ መስሎኝ ያላስተዋልኩትን አምላኬ አሳስበኝ አዝ:- ልጄ ሆይ አትሞኝ ስራህን አውቃለሁ ምን እንደጐደለህ እኔ እነግርሃለሁ ነፍሴን ደስ ልታሰኝ ከሆነ የአንተ ጉዳት ቀዳሚ ትዛዜን ፍቅሬን አስቀድማት ደጋግሞ በመጾም ሥጋዬን ጐድቼ ጉልበቴ እስኪሻክር በጸሎት ተግቼ አጣሁ ብመለከት ከዋና ቆርሼ ህመም ለጐበኘው በጸሎት ደርሼ ለእምነቱ ተጋዳይ ተብዬ እስክጠራ ስላንተ ተሰደድኩ ከሐዋርያት ጋራ ብዬ የኔንም ታሪክ እንደ ደመደምኩኝ ነፍስ የምትመረምር አንዴ ድምጽ ሰማሁኝ አዝ:- ልጄ ሆይ አድምጠኝ ስራህን አውቃለሁ ምን እንደጐደለህ እኔ እነግርሃለሁ ነፍሴን ደስ ልታሰኝ ከሆነ የአንተ ጉዳት ቀዳሚ ትዛዜን ፍቅሬን አስቀድማት
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection