ጠላቴ ዘርግቶ የወጥመድ ገመዱን እንቅፋት አኑሮ ዘግቶብኝ መንገዱን መድህኔን ፈልጌ ባቀና አይኖቼን አምላክ ደረሰልኝ አጸና እግሮቼን አዝ:- በክብር በሞገስ በዙፋኑ ሆኖ በምድር በሰማይ የሚኖረው ገኖ ከማንም ከማንም እርሱ ያስብልኛል የቀራንዮ ፍቅርህ ይንከባከበኛል አሜን የቀራንዮ ፍቅርህ ይንከባከበኛል የምወድህ ጌታ የምትወደኝ በቀራንዮ ስቃይ የዋጀኽኝ ደጋግሜ ላንተ እሰግዳለሁ በጸናችው ክንድህ እታመናለሁ ከኃጢአት አመድ ውስጥ እያየሁ አበሳ አይኖቼ ታውረው ስኖር በዳበሳ ትቢያዬን ከላዬ እፍ ብሎ አብሶ አቀፈኝ ጌታዬ ምህረትን አልብሶ አዝ:- በክብር በሞገስ በዙፋኑ ሆኖ በምድር በሰማይ የሚረው ገኖ ከማንም ከማንም እርሱ ያስብልኛል የቀራንዮ ፍቅርህ ይንከባከበኛል አሜን የቀራንዮ ፍቅርህ ይንከባከበኛል የምወድህ ጌታ የምትወደኝ በቀራንዮ ስቃይ የዋጀኽኝ ደጋግሜ ላንተ እሰግዳለሁ በጸናችው ክንድህ እታመናለሁ ለኑሮዬ ትርጉም በሮ ማረፊያዬ ሆንክልኝ ኢየሱስ ለኔ . (1) . መልሼ ልድገመው ተባረክ ጌታዬ ጊዜ የማይለውጥህ ታማኝ ጓደኛዬ አዝ:- ጌታ ኢየሱስ በአንተ ነፍሴ ደስ ይላታል የአንተ ፍቅር በእርግጥ በእርግጥ አርክቷቷል የሚጣፍጥ ኑሮ ጌታ አስለምዶኛል ካለ ኢየሱስ ላልኖር ልቤ ቆርጦልኛል (2x) የምወድህ ጌታ የምትወደኝ በቀራንዮ ስቃይ የዋጀኽኝ ደጋግሜ ላንተ እሰግዳለሁ በጸናችው ክንድህ እታመናለሁ