Song Lyrics

በአንተ ብዙ አልፌአለሁ

Addisu Worku
Ande Kortenal
በመቁሰሌ እየተሳለቁ ሳዝን ከእኔ እየራቁ ጨከኑ እርዳታ እንዳልጠይቅ ርቀዉኝ ፈጥነው ከእኔ ተነጠቁ አደሙ ከቶ እኔ ግን አልተረሳሁም አምላኬ ከክብሩ ሆኖ አሰበኝ ልቡ ራርቶልኝ በፍቅሩ ፈዋሽ እጆቹን ዘርግቶ ታደገኝ አዝ:- በአንተ አምላኬ ብዙ አልፌያለሁ ክንድህን ተማምኜ ተደግፌሃለሁ በአንተ ጌታ ብዙ አልፌያለሁ ክንድህን ተማምኜ ተደግፌሃለሁ የወጣት ጉልበቴን አፍስሼ ሃሳብ ዘወትር ተንተርሼ ዘመኔን የሰበሰብኩት ተበተነ የተማመንኩት ተነነ ዞር ስል ሰላም ፈልጌ ምድርም ሽቶኝ ቆይቼ የ እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት የጭንቀት ጩኽቴ ተሰምቶ አምላኬ ዘምበል ሲል አየሁት አዝ:- በአንተ አምላኬ ብዙ አልፌያለሁ ክንድህን ተማምኜ ተደግፌሃለሁ በአንተ ኢየሱስ ብዙ አልፌያለሁ ክንድህን ተማምኜ ተደግፌሃለሁ ባጣ ባጣ ሁሉ ባይረባኝ ከሁሉ የምትበልጠውን ጌታዬን ስላገኘሁ ክብር ይሰማኛል ጓደኝነጥትህ ያረካታል ሕይወቴን ዘመኔን ለእጅህ እሰጣለሁ ሕይወቴን በእግርህ ስር ጌታ አኖራለሁ አንተ አደራ የማትበላ ታማኝ ወዳጅ መሆንህን ሰምቻለሁ አዝ:- በአንተ አምላኬ ብዙ አልፌያለሁ ክንድህን ተማምኜ ተደግፌሃለሁ በአንተ ጌታ ብዙ አልፌያለሁ ክንድህን ተማምኜ ተደግፌሃለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection