Song Lyrics

ጌታን አምነዋለሁ

Addisu Worku
Ande Kortenal
ምን ይሆን እድሌ ምን ይገጥመኝ ይሆን ብዬ አልጨነቅም ያልፈቀድከው ላይሆን የነፍሴ ጠባቂ እንዳይተኛም ካለው በአምላኬ ታምኜ ጉዞ እጀምራለሁ አምነዋለሁ ጌታን አምነዋለሁ (2x) ጌታን አምነዋለሁ አዝ:- በማለዳም እነሳለሁ አምላኬን አነግሠዋለሁ ምስጋናዬን እሰዋለሁ ውለታውን አስታውሰዋለሁ ጌታን አመልካለሁ ደረቅ ምድረ በዳ እንደወደቀ እርጉም አስታዋሽ አጥቼ ለሞት አልተጣልኩም በመከራዬ ቀን ብቻውን ያሰበኝ ለልቤ ማረፊያ አፍቃሪ አምላክ አለኝ አምላክ አለኝ አፍቃሪ አምላክ አለኝ (2x) ጌታ ኢየሱስ አለኝ አዝ:- በማለዳም እነሳለሁ አምላኬን አነግሠዋለሁ ምስጋናዬን እሰዋለሁ ውለታውን አስታውሰዋለሁ ጌታን አመልካለሁ የህልውናን ምንጭ ህልውናን ክደው ሞት የተዛመዱ ከመንገድህ ርቀው ባያውቁት ነው እንጂ ያደረግክላቸው ሊከፍሉት የማይችሉት ውለታ አለባቸው አለባቸው ውለታህ አለባቸው (2x) ውለታህ አለባቸው አዝ:- በማለዳም እነሳለሁ አምላኬን አነግሠዋለሁ ምስጋናዬን እሰዋለሁ ውለታውን አስታውሰዋለሁ ጌታን አመልካለሁ ጀንበር ሊጠልቅ ነው ብዬ አልረበሽም እድል አመለጠኝ ብዬ ተስፋ አልቆርጥም አምላኬ እስካስቻለኝ ደረስ እጓዛለሁ በጐደለኝ ጌታ እንዲሞላው አውቃለሁ አመነዋለሁ ጌታን አመነዋለሁ (2x) ጌታን አምነዋለሁ አዝ:- በማለዳም እነሳለሁ አምላኬን አነግሠዋለሁ ምስጋናዬን እሰዋለሁ ውለታውን አስታውሰዋለሁ ጌታን አመልካለሁ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection