የድልን ጐዳና ሊያሳየኝ ብሎ ነው እስከመጨረሻው በአምላኬ ታምኜ ጌታን አየዋለሁ ምድር አፋፍ ላይ ሆኜ አዝ:- ጌታ በሚያስችለኝ ሁሉን እችላለሁ የማታ የማታ ድሌን አገኛለሁ ጌታ በሚያስችለኝ ሁሉን እችላለሁ የማታ የማታ ድል እቀዳጃለሁ ጊዜው ቢቆርቁር አንጀቴ ቢባባ ልቤ ቢርድብኝ ዓይኔ ቢያዝል እንኳ ሞትን ድል የነሳው ዛሬም ድል የእርሱ ነው ከእቅፉ ፈልቅቆ የሚጐዳኝ ማነው አዝ:- ጌታ በሚያስችለኝ ሁሉን እችላለሁ የማታ የማታ ድሌን አገኛለሁ ጌታ በሚያስችለኝ ሁሉን እችላለሁ የማታ የማታ ድል እቀዳጃለሁ ተስፋሽ አምላክሽ ነው ነፍሴ ሆይ አትፍሪ አምላክ ደጀኔ ነው ብለሽ ተናገሪ መከታሽ ከሆነ የጌቶቹ ጌታ በዓለም አይገኝም አንቺን የሚረታ አዝ:- ጌታ በሚያስችለኝ ሁሉን እችላለሁ የማታ የማታ ድሌን አገኛለሁ ጌታ በሚያስችለኝ ሁሉን እችላለሁ የማታ የማታ ድል እቀዳጃለሁ በጐደለኝ ነገር አምላክ ነው ሙላቴ በጥማቴ እርካታ በድካም ብርታቴ ከመጪው ፈተና እንዲያስጥለኝ አውቃለሁ ባያደርገው እንኳን ከእርሱ ጋር እሞታለሁ አዝ:- ጌታ በሚያስችለኝ ሁሉን እችላለሁ የማታ የማታ ድሌን አገኛለሁ ጌታ በሚያስችለኝ ሁሉን እችላለሁ የማታ የማታ ድል እቀዳጃለሁ