Song Lyrics

ህዝቤን ስጠኝ

Addisalem Assefa
Yamelete Ene Negn
ጌታዬና አምላኬ አንተ የልቤ ሆይ (2x) አንዴ አስበኝና ማዳንህን ልይ (2x) ክንድህ ወዴት አለ . (1) . የሚለኝ (2x) ለህዝብህ ጥያቄ ባክህ መልስ አርገኝ (2x) አዝ፦ ኢየሱስ ክብርህ ራበኝ (2x) አምላኬ ክብርህ ራበኝ እንጀራ እንደሆነ ጠግቤያለሁኝ የምድርን ቋጠሮ እባክህ ፍታልኝ (2x) ምነው ብትወርድ ምነው ብትፈርድ ለሃገሬ ለምድሬ የፈሰሰው እንባ ቢታበስ የፈረሰው ቅጥር ቢታደስ ምነው ብትወርድ ምነው ብትፈርድ ለሃገሬ ለምድሬ ተራራው በፊትህ ቢናወጥ ስምህ ለጠላቶች ቢገለጥ መልሰኛ ፈውስ አድርገህ ለሃገሬ ህመምተኛ ቀድሰኛ እንድሆን የወንጌል አርበኛ ተቆጥተህ ፊትህን አትደብቅብኝ ደክሞኝ ሳለ ጠላቴ እንዳይወድቅብኝ በፈረሰው ቅጥር የቆመ ለእንጀራ ያልኖረ (2x) የቤትህ ቅናት የሚበላው ስሙን . (2) . (2x) የልብህን ቁጣ ትኩሳት የሚያበርድልህ (2x) እንዲህ ዐይነት ጨካኝ ሰው አድርገኝ ኃይልህን ሞልተህ (2x) ከዚያ በኋላማ ስምህን አክብረህ ትመላለሳለህ መስርአት ሳይከብድህ አዝ፦ ኢየሱስ ክብርህ ራበኝ (2x) አምላኬ ክብርህ ራበኝ እንጀራ እንደሆነ ጠግቤያለሁኝ የህዝቤን/የምድሬን ቋጠሮ እባክህ ፍታልኝ (2x) ምነው ብትወርድ ምነው ብትፈርድ ለሃገሬ ለምድሬ የፈሰሰው እንባ ቢታበስ የፈረሰው ቅጥር ቢታደስ ምነው ብትወርድ ምነው ብትፈርድ ለሃገሬ ለምድሬ ተራራው በፊትህ ቢናወጥ ስምህ ለጠላቶች ቢገለጥ መልሰኛ ፈውስ አድርገህ ለሃገሬ ህመምተኛ ቀድሰኛ እንድሆን የወንጌል አርበኛ ተቆጥተህ ፊትህን አትደብቅብኝ ደክሞኝ ሳለ ጠላቴ እንዳይወድቅብኝ በምድሬ እንዳትሰራ እንዳትከብር የከለከልኩኝ (2x) አንካሳ የሕይወት ማንነት ያለኝ እኔ ነኝ (2x) አሁን ግን በምህረት ዐይንህ አይተኸኝ (2x) የተጨነቀውን ህዝብህን ስጠኝ (2x) ኢየሱስ እባክህ ነክቼህ ንካኝ ኃይልህ እስኪወጣ ልበልህ ሙጥኝ አዝ፦ ኢየሱስ ክብርህ ራበኝ (2x) አምላኬ ክብርህ ራበኝ እንጀራ እንደሆነ ጠግቤያለሁኝ የህዝቤን/የምድሬን ቋጠሮ እባክህ ፍታልኝ (2x) ህዝቤን ስጠኝ እንደፈቃድህ አውለኸኝ ህዝቤን ስጠኝ ህዝቤን ስጠኝ በቅድስናህ አውለከኝ ህዝቤን ስጠኝ ህዝቤን ስጠኝ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection