Song Lyrics

የራራልኝ

Addisalem Assefa
Yamelete Ene Negn
ከልጅነቴ ጀምሮ እጄን አጥብቆ የያዘኝ ዘር ባልተዘራበት ምድረ በዳ በፍቅሩ ያባበለኝ ጊንጡን ረጋግጦልኝ እባቡም እንዳይነድፈኝ እንባዬን በእጁ ጠራርጐ አባት ልሁንሽ ያለኝ አዝ፦ የራራልኝ የደገፈኝ ሰዎች ሲረሱኝ ያስታወሰኝ ዛሬም ሊረዳኝ መች ይሰለቸዋል በእርሱ ተረድቶ ማን ወድቆ ያውቃል (2x) ይችላል ይችላል ብያለሁ በነገሬ ላይ ቃል ከአፉ ይውጣ እንጂ ከሠማይ የሞተው ይነሳል የለም ወይ ይችላል ይችላል ብያለሁ በነገሬ ላይ ቃል ከአፉ ይውጣ እንጂ ከሠማይ አልአዛርስ ቆሞ የለም ወይ በአመት መሃል ሁል ጊዜ የማይለወጥ ደግ ጌታ ተስፋ ሲጨልም ቀን ሲመሽ የሚድል ሲል ማታ ማታ ስሙን ጠርቼ አላፈርኩ አንገቴን አልደፋሁ በዘመኔ ህይው ምስክር ያረገኝ ሳይርቀኝ ቆሞ ከጐኔ አዝ፦ የራራልኝ የደገፈኝ ሰዎች ሲረሱኝ ያስታወሰኝ ዛሬም ሊረዳኝ መች ይሰለቸዋል በእርሱ ተረድቶ ማን ወድቆ ያውቃል (2x) ይችላል ይችላል ብያለሁ በነገሬ ላይ ቃል ከአፉ ይውጣ እንጂ ከሠማይ የሞተው ይነሳል የለም ወይ ይችላል ይችላል ብያለሁ በነገሬ ላይ ቃል ከአፉ ይውጣ እንጂ ከሠማይ አልአዛርስ ቆሞ የለም ወይ የደረቀ አጥንት ነው ግን ለእግዚአብሔር ቀላል ነው የሸተተ ሬሳ ነው ግን ለእግዚአብሔር ቀላል ነው ትቼዋለሁ ቀብሬው ግን ለእግዚአብሔር ቀላል ነው ያወጣዋል በጊዜው አው ለእግዚአብሔር ቀላል ነው መርከብ ተሰብሮ በተሰበረው መድረስ ከቻለ ያ የእምነት ሰው ዛሬም በቤቴ ይሄ ይሆናል አልጠረጥርም እርሱ ይችላል አልጠረጥርም እርሱ ይችላል አልጠረጥርም ጌታ ይችላል አልተረጥርም ጌታ ይችላል አልጠረጥርም እርሱ ይችላል አዝ፦ የራራልኝ የደገፈኝ ሰዎች ሲረሱኝ ያስታወሰኝ ዛሬም ሊረዳኝ መች ይሰለቸዋል በእርሱ ተረድቶ ማን ወድቆ ያውቃል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection