Song Lyrics

ከአፌ የማይጠፋው

Addisalem Assefa
Yamelete Ene Negn
አዝ፦ ከአፌ የማይጠፋ የማልረሳው የማልረሳው ከአፌ የማይጠፋው የማልተወው የማልተወው ከየት እንዳነሳኝ ነው (4x) አለኝ ብዙ ምሥጋና ለጌታዬ አለኝ ብዙ ምሥጋና ደግሜ ደግሜ እንደገና ደግሜ ደግሜ እንደገና ደግሜ ደግሜ እንደገና ደግሜ ደግሜ እንደገና (2x) በሕይወት ለመኖር የሚያስችለኝ ከሠማይ ትዕዛዝ ወጥቶልኝ ነው እንጂ በቤቱ መዘመቴ መቼ በህይልና በብርታቴ አሃ በብርታቴ እርሱ ነው ከደሜ ያጠራኝ አፍረቴን ሸፍኖ ያነሳኝ እርቃኔን በ. (1) . አስሬው ደብቆ ያከበረኝ እርሱ ነው አሃ እርሱ ነው አዝ፦ ስለዚህ . (2) . አልፈልግም አምላኬን ለማመስገን ጌታዬን ለማመስገን በእርሱ እኮ ነው የተሻገርኩት ያለፍኩት ያንን ክፉ ቀን (2x) አለኝ ብዙ ምሥጋና ለጌታዬ አለኝ ብዙ ምሥጋና ደግሜ ደግሜ እንደገና ደግሜ ደግሜ እንደገና (2x) በንጉሥ ገበታ ተቀምጬ ከሕይወት እንጀራው እንድበላ ንጉሥ ለሚወደው እንዲህ ይሁን ተብሎ ሲነገር ሲወራ (2x) በትልቁ እግዚአብሔር ተወድጄ ከውዳቂ ስፍራ ተነስቼ በፊቱ ልቆም ዘንድ እኔ ማን ነኝ እስከዚህ ነው ለካ የወደደኝ አሃሃ የወደደኝ ስለዚህ . (2) . አልፈልግም አምላኬን ለማመስገን ጌታዬን ለማመስገን በእርሱ እኮ ነው የተሻገርኩት ያለፍኩት ያንን ክፉ ቀን (2x) አዝ፦ ከአፌ የማይጠፋ የማልረሳው የማልረሳው ከአፌ የማይጠፋው የማልተወው የማልተወው ከየት እንዳነሳኝ ነው (4x) አለኝ ብዙ ምሥጋና ለጌታዬ አለኝ ብዙ ምሥጋና ደግሜ ደግሜ እንደገና ደግሜ ደግሜ እንደገና (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection