Song Lyrics

ጆሮዬን ልብሳ

Joreyen Libesa

Addisalem Assefa
Special Edition
ሃጥያት አላገኘህም ስንፍና አልከሰሰህም ስትገዛ አልደከመህም እርጅና አላወቀህም(፪) እኔም አላውቅህም የዘመንህ ቁጥር አይመረመርም(፪) እኔም አላውቅህም የዘመንህ ቁጥር አይመረመርም(፪) የለህም እኩያ የለህም አምሳያ ትልቅ ነህ ሃሌሉያ(፪) ትልቅ ነህ ሃሌሉያ(፬) የነገሥታት ወገብ ትጥቅ የምታስፈታ ሓያል አምላክ የጌቶች ጌታ(፫) የፍጥረት መገኛ ሕያው መሠረት አትሰላ በዓመታት አትደመር በዘመናት አትሰላ በዓመታት የትኛውም ምሑር ሒሳብ አይሰራህም የትኛውም ሰዓሊ ብሩሽ አይቀባህም የቱም አንጠረኛ ቀርጾ አያወጣህም አሐዱ አትባልም ደረጃም የለህም ኧረ እኔስ ለክብርህ ኧረ እኔስ ለዝናህ ሽርጉድ ልበል ላገልግልህ ጆሮዬን ልብሳ ልኑልርህ(፪) ልኑርልህ(፬) እስቲ የማን ጀግና ሞትን አሸነፈ እስቲ የማን ጀግና ጨለማ ገፈፈ እስቲ የማን ጀግና ሲዖልን ድል ነሳ ኢየሱስ ብቻ ነህ የይሁዳ አንበሳ ኢየሱስ ብቻ ነህ ጀግና ኢየሱስ ብቻ ነህ ኢየሱስ ብቻ ነህ ጀግና ዙፋንህ የጸና ኢየሱስ ብቻ ነህ ጀግና ኢየሱስ ብቻ ነህ ኢየሱስ ብቻ ነህ ጀግና ዙፋኑ የጸና ዙፋንህ የጸና (፪x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection