Song Lyrics

ምስክር ነበረ

Addisalem Assefa
Special Edition
ያሳብቅብኛል እነበባለሁ የአንተ ምህረት በላዬ ላይ ነው ያሳብቅብኛል እነበባለሁ የአንተ ቸርነት በላዬ ላይ ነው ስትረዳኝ ምስክር ነበረ ምህረትህ ስታነሳኝ ምስክር ነበረ ደግነትህ ስትረዳኝ ምስክር ነበረ ምህረትህ ስታነሳኝ ምስክር ነበረ ደግነትህ እነ እውነትና እነ ፍቅርህ ተሸክመውኝ አለው ቤትህ እነ እውነትና እነ ፍቅርህ ይቅር ብለውኝ አለው ደጅህ ሳልወደድ የወደድከኝ ሳልቆጠር እንደሰው ወደ እኔ የመጣህበት መልካምነት ልክ የለው ትልቅ ሆነህ ሳትንቀኝ ወደ ቤቴ ከመጣህ እኔም አለኝ ብርቱ መስዋት ደራርቤ የምሰጥህ መሰወር እንዴት ይሆንልኛል ያነሳኝ እጅህ ይታዘበኛል መደበቅ እንዴት ይሆንልኛል ምህረትህ ከቦኝ ያዘምረኛል የቋንቋዬ ጉልበት የእውቀቴ ልቀት ተስማምተው ቢያወሩ በጥኡም አንደበት ቢፅፉት በቀለም በህግ ቢያትሙት ማለዳ አዲስ ነው የአንተ ምህረት ያሳብቅብኛል እነበባለሁ የአንተ ምህረት በላዬ ላይ ነው ያሳብቅብኛል እነበባለሁ የአንተ ቸርነት በላዬ ላይ ነው ስትረዳኝ ምስክር ነበረ ምህረትህ ስታነሳኝ ምስክር ነበረ ደግነትህ ስትረዳኝ ምስክር ነበረ ምህረትህ ስታነሳኝ ምስክር ነበረ ደግነትህ እነ እውነትና እነ ፍቅርህ ተሸክመውኝ አለው ቤትህ እነ እውነትና እነ ፍቅርህ ይቅር ብለውኝ አለው ደጅህ በደም ተለውሼ ሳለው ሰው ሳያየኝ አይተኸኝ አትሙቺ ብለኸኝ በአፍህ ቃል ያኖርከኝ ከቶ ላትችል ልትረሳኝ በስምህ የማልክልኝ ቸር መምህሬ ስለአንተማ የማወራው ብዙ አለኝ መሰወር እንዴት ይሆንልኛል ያነሳኝ እጅህ ይታዘበኛል መደበቅ እንዴት ይሆንልኛል ምህረትህ ከቦኝ ያዘምረኛል የቋንቋዬ ጉልበት የእውቀቴ ልቀት ተስማምተው ቢያወሩ በጥኡም አንደበት ቢፅፉት በቀለም በህግ ቢያትሙት ማለዳ አዲስ ነው የአንተ ምህረት ያሳብቅብኛል እነበባለሁ የአንተ ምህረት በላዬ ላይ ነው ያሳብቅብኛል እነበባለሁ የአንተ ቸርነት በላዬ ላይ ነው ስትረዳኝ ምስክር ነበረ ምህረትህ ስታነሳኝ ምስክር ነበረ ደግነትህ ስትረዳኝ ምስክር ነበረ ምህረትህ ስታነሳኝ ምስክር ነበረ ደግነትህ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection