አንድ ነገር በጣም ገብቶኛል በሕይወት ዘመኔ የዛለው በአንተ ሲበረታ አይቻለሁ በዓይኔ ተቆትተህ በዛው አትቀርም እስከ መጨረሻው ቢወድቅም ይነሳል ፃዲቁ ስላለው . (1) . አዝ፦ ስንት ጊዜ አነሳኸኝ ስንት ጊዜ አቅም ሆንከኝ ስንት ጊዜ ጨለማዬን ከደንከው በብርሃን ስንት ጊዜ ስደክምብህ ስንት ጊዜ ያዘኝ ፀጋህ ስንት ጊዜ ከጠላት ዛቻ ከለለኝ ምህረትህ ብቻ (5x) ያንን ጭጋግ ደመናውን ያን በረሃ ሃሩር በአንተ ጉልበት አልፌዋለሁ በማሳለፍ እንደ አንተ ማነው ያን ኃጢያቴን ቁሻሻውን ያንን ልብሴን እድፋሙን ቀይረህ ከሞት ወጥቻለሁ በማሳጣት እንደ አንተ ማነው አዝ፦ ስንት ጊዜ አነሳኸኝ ስንት ጊዜ አቅም ሆንከኝ ስንት ጊዜ ጨለማዬን ከደንከው በብርሃን ስንት ጊዜ ስደክምብህ ስንት ጊዜ ያዘኝ ፀጋህ ስንት ጊዜ ከጠላት ዛቻ ከለለኝ ምህረትህ ብቻ (5x) ምህረትህ በዝቶልኝ ነው እንጂ ማነሳሳህ ደጋግሜ በተከበበው ከተማማ ለእኔ ይገርመኛል መቆሜ ስለዚህ በምሥጋና ልውጣ ያረክልኝን ቆጥሬ ሳላስበው ከአንተ ጋራ . (2) . ከብሬ አዝ፦ ስንት ጊዜ አነሳኸኝ ስንት ጊዜ አቅም ሆንከኝ ስንት ጊዜ ጨለማዬን ከደንከው በብርሃን ስንት ጊዜ ስደክምብህ ስንት ጊዜ ያዘኝ ፀጋህ ስንት ጊዜ ከጠላት ዛቻ ከለለኝ ምህረትህ ብቻ (5x) አባትዬ ኢየሱስዬ አልከሰርኩም እኔ አንተን ብዬ እኔ አንተን ብዬ (2x) እኔ አንተን ብዬ (4x)