Song Lyrics

አልወርድም

Addisalem Assefa
Yamelete Ene Negn
አስገረመኝ/አስደነቀኝ ነገሬን ውብ አረገና አፌን ሞላው በአዲስ ቅኔ በምሥጋና በዝማሬ እገባለሁ ወደ ቤቱ ሥራዬ ተሰርቷልና በምረቱ ኃይሌን አድሶት ጌታዬ ወጥቻለሁ አሃሃ ነቅቻለሁ ከዚያ ላይ ማን ያወርደኛል ከፍ ብያለሁ አሃሃ ከፍ ብያለሁ ጠላቴ አታገኘኝም በትላንቱ በትላንቱ ኢየሱስ መጥቶ አውጥቶኛል በሰዓቱ በሰዓቱ በሰዓቱ በሰዓቱ (፬x) የማታ ለቅሶዬ ጠዋት ተለውጦ እንደ መርደኪዮስ ታሪክ ነገር ተገልብጦ በኮረብታ ሆኜ መዝሙር ዘምራለሁ ሆ እኔ ከላይ ሆኜ ጠላቴን ረግጫለሁ አልወርድም ከከፍታዬ ላይ እግዚአብሔር አርጐኛል የበላይ ዝቅታው ያንተ ነው ጠላቴ እግዚአብሔር ጥሎሃል ከፊቴ እግዚአብሔር ቀኑን እስኪሰጥ ድረስ አይኔ ዝም ብሎ እምባን ቢያፈስ እንዳለቀስኩኝ መቼ ቀረሁኝ የምስቅበት ዘመን መጣልኝ አፌን ምሥጋና ኦሆ ይኸው ሞላኝ ( 2x) አልወርድም ከከፍታዬ ላይ እግዚአብሔር አርጐኛል የበላይ ዝቅታው ያንተ ነው ጠላቴ እግዚአብሔር ጥሎሃል ከፊቴ የእግዚአብሔር ጉልበት የክንዱ ብርታት ይህንን አድርጓል ሰርቶ ታምራት ክፉ በሆኑት ቀናቶች ፈንታ ደስታ አጠገበኝ ኤልሻዳዩ ጌታ አመልከዋለሁ ሁሌ ጠዋት ማታ ( 2x) ኃይሌን አድሶት ጌታዬ ወጥቻለሁ አሃሃ ነቅቻለሁ ከዚያ ላይ ማን ያወርደኛል ከፍ ብያለሁ አሃሃ ከፍ ብያለሁ ጠላቴ አታገኘኝም በትላንቱ ኦሆሆ በትላንቱ ኢየሱስ መጥቶ አውጥቶኛል በሰዓቱ ኦሆሆ በሰዓቱ በሰዓቱ በሰዓቱ (፬x) ልቤን አልጥልም ከጠፉት አህዮች ላይ እግዚአብሔር መጥቷል ሊሰጠኝ ከዚያ በላይ ሃሳቡ ለእኔ ምንጊዜም የመልካም ነው ታምር ሲሰራ በሕይወቴ አይቻለሁ አልወርድም ከከፍታዬ ላይ እግዚአብሔር አርጐኛል የበላይ ዝቅታው ያንተ ነው ጠላቴ እግዚአብሔር ጥሎሃል ከፊቴ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection