Song Lyrics

ቀንበር ሰብሮ

Addisalem Assefa
Sebariw Geta Kefite Wetoal
አዝ፦ ቀንበር ሰብሮ እስራትን የሚፈታ አሃሃሃ ማን እንደ ጌታ ማን እንደኢየሱስ ማን እንደጌታ ከፍ የሚያደርግ አንስቶ ከውርደት ቦታ አሃሃሃ ማን እንደጌታ ማን እንደ ኢየሱስ ማን እንደጌታ ለዚህ ጌታ እሰግድለታለሁ ተሸክሞኝ እዚህ ደርሻለሁ ለዚህ ንጉሥ እቀኝለታለሁ በእርሱ ብርታት ዛሬን አይቻለሁ ምስኪን ችግረኛን እንደማንም ሳይተው እንደ ባለማዕረግ ስፍራን የሚሰጠው የወደቀን ማንሳት ክብር የሆነለት መታሰቢያም ሚያቆም ሰርቶ ታምራት ባርኮ እየባረከ በእርሱ ደግነት አክብሮ የሚያኖር ነው መልካም አባት (2x) አዝ፦ ቀንበር ሰብሮ እስራትን የሚፈታ አሃሃሃ ማን እንደ ጌታ ማን እንደኢየሱስ ማን እንደጌታ ከፍ የሚያደርግ አንስቶ ከውርደት ቦታ አሃሃሃ ማን እንደጌታ ማን እንደ ኢየሱስ ማን እንደጌታ ለዚህ ጌታ እሰግድለታለሁ ተሸክሞኝ እዚህ ደርሻለሁ ለዚህ ንጉስ እቀኝለታለሁ በእርሱ ብርታት ዛሬን አይቻለሁ ምሕረቱን አብዝቶ ሞገስ የሚሰጥ የጠላትን ከፍታ ወስዶ ሚያስረግጥ በክንፎቹ ጥላ ሸሽጎ የሚያኖር ተማምኖ ለተራው ስሙን የሚያከብር እጅግ የሚራራ የበዛ እርዳታው እንደ እግዚአብሔር ያለ ደግ አምላክ ማን ነው (2x) አዝ፦ ቀንበር ሰብሮ እስራትን የሚፈታ አሃሃሃ ማን እንደ ጌታ ማን እንደ ኢየሱስ ማን እንደጌታ ከፍ የሚያደርግ አንስቶ ከውርደት ቦታ አሃሃሃ ማን እንደጌታ ማን እንደ ኢየሱስ ማን እንደጌታ ለዚህ ጌታ እሰግድለታለሁ ተሸክሞኝ እዚህ ደርሻለሁ ለዚህ ንጉስ እቀኝለታለሁ በእርሱ ብርታት ዛሬን አይቻለሁ ከፍ ከፍ ይበል የእኔ ጌታ ከፍ ከፍ ይበል ከፍ ከፍ ይበል የእኔ ወዳጅ ከፍ ከፍ ይበል እንደሱ ጌታ እስቲ የታል (2x) እንደሱ ፍቅር እስቲ የታል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection