Song Lyrics

እግዚአብሔር መልካም ለእኔ

Addisalem Assefa
Sebariw Geta Kefite Wetoal
አዝ፦ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ (2x) ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ (2x) ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ (2x) ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ (2x) በወይን ሐረግ ዛላ ፍሬ ባይገኝ ባይኖር የሚረዳ ከግራ ከቀኝ በለሷን ጠብቄ ፍሬን እበላለሁ ቀኝ እጄን የያዘኝ መቼ ሊረሳኝ ነው እሱን ታምኖ ጠርቶ ከቶ ማንስ አፍሯል ይልቁን በስሙ ቀንዱ ከፍ ብሏል እኔም በስሮቼ ከፍ ከፍ እላለሁ አለኝ የሚረዳ ይህንን አውቃለሁ (3x) አዝ፦ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ (2x) ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ (2x) ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ (2x) ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ (2x) ጨለማው በርትቶ ማይነጋ ሲመስል ዮርዳኖስም ሞልቶ አላሻግርም ሲል ታምራት አድርጎ ያሻገረው ጌታ እግዚአብሔር መልካም ነው ዛሬም በእኔ ቦታ ሞትን ያሸነፈ ድል የነሳ ጌታ ሰባቱን ማህተም ተርትሮ የፈታ ዛሬም በቸርነት ይከታተለኛል እሱን ተደግፌ ምንስ ያሰጋኛል (3x) አዝ፦ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ (2x) ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ (2x) ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር መልካም ለእኔ (2x) ሁልጊዜ በዘመኔ እግዚአብሔር በጐ ለእኔ (2x) ወረት የለበትም ፍቅሩ ሁሌ ስያፈቅር ይኖራል መንገድ አስጀምሮ ጉዞ መች እዚህ አውጥቶ ይሄዳል እቅፍ ድግፍ አርጎ ይዞ በብዙ ሞገስ ያኖራል ላይተው ላይረሳ በራሱ በስሙ ኪዳን ይምላል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection