ተጨንቃ ለነበረች ነፍሴ ጨለማን አይሆንም ሲል አዋጅን በአዋጅ ሽሮ መርዶዬን ሲከለክል ከፊቴ ቀድሞ ሲወጣ ተራራን ሲደለድል ሥራዬን ሰርቶ ሲጨርስ ችግሬን ሲጠቀልል መቃብሬን ሲከፍተው ታምር ሲሰራ ነፍሴን እጅግ ሲያስጨንቅ በእኔ ሲፈራ ታምራት ሲያስለምደኝ ሲያሳየኝ ኖሬ እንዴት እሸበራለሁ እፈራለሁ ዛሬ አዝ፦ እንዴት እንዴት እፈራለሁ (3x) ለምን ለምን እሰጋለሁ (3x) የተሸከመኝ ትልቅ አምላክ ነው (4x) ስንቱን ሸለቆ ስንቱን ተራራ ጥሼ ሄጃለሁ ከእርሱ ጋራ (2x) እያሪኮዬ ቅጥሩ ሲፈርስ አይታለች ነፍሴ በኢየሱስ (2x) ስለዚህ አልፈራም ምድር ብትናወጥ በዙፋኑ እያለ ከቶ ከቶ ማይናወጥ (2x) በዙፋኑ እያለ ከቶ ከቶ ማይናወጥ (2x) አዝ፦ እንዴት እንዴት እፈራለሁ (3x) ለምን ለምን እሰጋለሁ (3x) የተሸከመኝ ትልቅ አምላክ ነው (4x) በእሳት ማሃል መንገድ ያለው ጌታ መቼ ትቶኝ ያውቃል አንድ አፍታ ማዕበልና ወጀቡን አራምዶ ያሻግረኛል ከባህር ማዶ ስለዚህ አልፈራም ምድር ብትናወጥ በዙፋኑ እያለ ከቶ ከቶ ማይናወጥ (2x) በዙፋኑ እያለ ከቶ ከቶ የማይናወጥ (2x) አዝ፦ እንዴት እንዴት እፈራለሁ (3x) ለምን ለምን እሰጋለሁ (3x) የተሸከመኝ ትልቅ አምላክ ነው (4x)