Song Lyrics

የጠበኩት ጌታ

Addisalem Assefa
Sebariw Geta Kefite Wetoal
የጠበኩት ጌታ ድንገት ይመጣል (2x) አሜን ድንገት ይመጣል ሁሉን ዉብ ያደርጋል የጠበኩት ጌታ ድንገት ይመጣል (2x) እሰይ ድንገት ይመጣል ሁሉን ዉብ ያደርጋል ዞር በል ጠላቴ አትነዝንዘኝ ዞር በልልኝ መቼ ሊረሳኝ ነው እግዚአብሔር አባት የሆነኝ ስንቱን አልፌያለሁ በእርሱ ብርታት በጀርባው አዝሎኝ አሁንም ታማኝ ነው የእኔ ጌታ ፈጥኖ ሊረዳኝ አልተውሽም ብሎ ተናግሮኛል እንደሱ እውነተኛ የት ይገኛል (2x) ያስጨበጠንኝ ቃል እየዛለሁ በቃሉ ይገኛል አምነዋለሁ በቃሉ ይገኛል አምነዋለሁ (2x) ድንገት ይመጣል (ድንገት ይመጣል) ድንገት ይመጣል አሜን ድንገት ይመጣል ሁሉን ይለውጣል (3x) ድንገት ሲመጣ አሃ አሃሃ ወደ መቅደሱ እምባን በማበስ አሃ አሃሃ ማነው እንደሱ ሰፍሬ አልፋለሁ አሃ አሃሃ የነሃሱን ደጃፍ መቆም አልሻም ከቶ ጌታ ስለሚያልፍ ድንገት ይመጣል (ድንገት ይመጣል) ድንገት ይመጣል አሜን ድንገት ይመጣል ሁሉን ይለውጣል ድንገት ይመጣል (ድንገት ይመጣል) ድንገት ይመጣል እሰይ ድንገት ይመጣል ሁሉን ይለውጣል እርሱን ብዬ የምን ጭንቀት እሱን ብዬ (እሱን ብዬ) ያለስጋት ልቀመጥ እንጂ ተዘልዬ (2x) ቢዘገይም እኮ በርግጥ ይመጣል (ይመጣል) ሁሉን ነገሬን አዲስ ያደርጋል (አዲስ ያደርጋል) በቀጠረው ሰዓት በራሱ ጊዜ (በራሱ ጊዜ) በእርሱ ይገሠጻል ሃዘን ትካዜ (2x) እሱን ብዬ የምን ጭንቀት እሱን ብዬ (እሱን ብዬ) ያለስጋት ልቀመጥ እንጂ ተዘልዬ (2x) ቢዘገይም እኮ በርግጥ ይመጣል (ይመጣል) ሁሉን ነገሬን አዲስ ያደርጋል (አዲስ ያደርጋል) በቀጠረው ሰዓት በራሱ ጊዜ (በራሱ ጊዜ) በእርሱ ይገሠጻል ሃዘን ትካዜ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection