Song Lyrics

ዘመን መጣ

Addisalem Assefa
Sebariw Geta Kefite Wetoal
ሞቴን በሕይወት ቀይሮ ነገሬን ሊገለብጥ በጭንቀቴ ሊያሰፋ ከፍታን ለእኔ ሊሰጥ አዎ ዘመን መጣ ከፊቴ ፋሬስ ብዬ የምጥስበት የያዘኝ ዳግም ላይዘኝ ሰብሬ የምወጣበት (2x) ሰባሪው ጌታ ከፊቴ ወጥቷል አማሌቅ ፈርቶ መንገዴን ለቋል ክረምቱ አልፎ ጭጋጉ በኗል ዛሬ ለእኔ የዜማ ጊዜዬ ሆኗል አምልኮ ይዤ ልምጣ እኔም በተራዬ (በተራዬ) (2x) ሌሊቱን በሚያነጋው ታብሷል እምባዬ (ታብሷል) (2x) አምልኮ ይዤ ልምጣ (ይዤ ልምጣ) እኔም በተራዬ (2x) ቀን ቀጥሮ በሚመጣው (በሚያነጋው) ታብሷል እምባዬ (2x) ከአለት ንቃቃት የምወጣበት እጄን በአፌ ላይ የምጭንበት የጠላቴን አፍ የሚዘጋበት ዘመን መጣ ይምከብርበት ከእንግዲህ በቃ ማልቀስ በሸለቆ የናሱም ደጃፍ ተበርግዷል አውቆ ልሂድ ልውረሰው ከቶ አታዘግዩኝ እግዚአብሔር ነው ውረሺው ያለኝ (2x) እግዚአብሔር ነው ውረሺው ያለኝ (4x) በቃ ሌሊቱ ነጋ በጠላቴ ላይ ተዘጋ ጌታ ቀኝ እጄን ይዞ አሻገረን ከእርሱ ጋር መንኮራኩሩ ታስሮ ተጨነቀ ጠላቴ እኔ ግን እየዘመርኩ ገባሁኝ ወደርስቴ የማንም እምባ ባለዕዳ አይደለም ጌታ ዘመናት ቆጥሮ ያቆማል በከፍታ (2x) ከፍ ይበል ጌታ ማህተሜን የፈታ (4x) አምልኮ ይዤ ልምጣ እኔም በተራዬ (በተራዬ) (2x) ሌሊቱን በሚያነጋው ታብሷል እምባዬ (ታብሷል) (2x) አምልኮ ይዤ ልምጣ (ይዤ ልምጣ) እኔም በተራዬ (2x) ቀን ቀጥሮ በሚመጣው (በሚያነጋው) ታብሷል እምባዬ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection