Song Lyrics

በኪሩቤል ላይ

Abraham and Eyasu
Zemenat Ayilewituhim
ከሰማያት በላይ በክብር ላለኸው ለሞትና ለሲዖል ኃይልህን ያስታወቅከው የዘላለም ደጆች ላንተ ይከፈቱ የጽድቅ ንጉሥ ግባ ዛሬም እንደ ጥንቱ አዝ:- በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ አንተ ታይ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ የሰላም አለቃ ኢየሱስ አንተ ና እንደተስፋ ቃልህ መጣህ ወደ ምድር ለገባው ሚስጥሩ ታየ የአንተ ክብር የማይሻር የጸና የትንቢት ቃል ይዘን እስክትመጣ ኢየሱስ እንጠብቅሃለን አዝ:- በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ አንተ ታይ በኪሩቤል ላይ የምትቀመጥ የሰላም አለቃ ኢየሱስ አንተ ና ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) በምሥጋና (በምሥጋና) እናንግሠው (እናንግሠው) አዝ:- በኪሩቤል ላይ (በኪሩቤል ላይ) የምትቀመጥ የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ አንተ ታይ በኪሩቤል ላይ (በኪሩቤል ላይ) የምትቀመጥ የሰላም አለቃ ኢየሱስ አንተ ና (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection