ምድርና ሞላዋን በቃልህ ያፀናህ በክብርህ ሞገስ በብርሃንህ ዓለምን የሞላህ እንዴት ላክብርህ ዛሬስ ምን ይዤ በፊትህ ልግባ አዲስ ምሥጋና አዲስ ዝማሬ አይበዛብህምና አዝ:- እጆቼን ወደ ሰማይ አንስቼ በንጹህ ልብ ዛሬም እስከ ዘለዓለም ላመስግነው አምላኬን በሰማይ ላለው ለኢየሱስ ቅኔ ልቀኝለት (2x) ታማኝነቱንም ገናናነቱንም አይቼ ስለ ምሕረትህ ባስብ ባወራ አመታት ያጥሩኛል አቤቱ ኢየሱስ የታምራትህ ዘርፍ እረዝሟልና ለነፍሴ ዘወትር ተሟግተሃል ሕይወቴንም በደምህ ተቤዥተሃልና አዝ:- እጆቼን ወደ ሰማይ አንስቼ በንጹህ ልብ ዛሬም እስከ ዘለዓለም ላመስግነው አምላኬን በሰማይ ላለው ለኢየሱስ ቅኔ ልቀኝለት (4x) ታማኝነቱንም ገናናነቱንም አይቼ በላይ በዙፋንህ ላይ በክብር ነግሰህ ታየህ አቤቱ (4x) (ክብር ይሁን) ላመስግነው አምላኬን በሰማይ ላለው ለኢየሱስ ቅኔ ልቀኝለት (2x) በላይ በዙፋንህ ላይ በክብር ነግሰህ ታየህ አቤቱ (ክበር ክበር መድኃኒቴ) በላይ በዙፋንህ ላይ በክብር ነግሰህ ታየህ አቤቱ (ክበር ንገሥ መድኃኒቴ)(2x) በላይ በዙፋንህ ላይ በክብር ነግሰህ ታየህ አቤቱ