Song Lyrics

በሚመራኝ እሄዳለው

Abraham and Eyasu
Zemenat Ayilewituhim
በሚመራኝ እሄዳለሁ ህይወቴን ሰጥቼዋለሁ አልረሳም አስታዉሳለሁ በሞቱ ተፈውሻለሁ አዝ:- በሌት በቀኔ ይመራኛል ኢየሱስ ያስፈልገኛል እውነተኛ ወዳጄ ነው ነፍሴን በደሙ የገዛው ትዕዛዝህን አከብራለሁ በክንድህ እደገፋለሁ ተስፋ ሳልቆርጥ እጓዛለሁ አንድ ቀን አዳኜን አየዋለሁ አዝ:- በሌት በቀኔ ይመራኛል ኢየሱስ ያስፈልገኛል እውነተኛ ወዳጄ ነው ነፍሴን በደሙ የገዛት አልተክዝም ከቶ አልፈራም አንተ ካለህ ከእኔ ጋራ ፍጹም ፍቅርህ መድኃኒቴ ማጽናኛ ነው ለሕይወቴ አዝ:- በሌት በቀኔ ይመራኛል ኢየሱስ ያስፈልገኛል እውነተኛ ወዳጄ ነው ነፍሴን በደሙ የገዛት አንዳንድ ጊዜ ፈተና ሲበዛ መከራ ችግር ቢበዛብን (ኧረ) አንድ እንኳ ቢታጣ የሚረዳ ኢየሱስ አለ ከእኛ ጋራ አንዳንድ ጊዜ ፈተና ሲበዛ (ሃሌሉያ) መከራ ችግር ቢበዛብን አንድ እንኳ ቢታጣ የሚረዳ (ቢታጣ) ኢየሱስ አለ ከእኔ ጋራ (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection