Song Lyrics

የሕይወት ውኃ

Abraham and Eyasu
Zemenat Ayilewituhim
በዚያም በታላቁ ቀን ኢየሱስ ቆሞ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ በእኔ የሚያምን መጽሐፉ እንዳለው የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ዛሬም ይሄ ነው ፀሎታችን የእምነት ቃሉን የሰጠ እስከ ፍጻሜው ታማኝ ነው የፍጥረት ሁሉ አባት ለልጆቹ የሚዋጋው እሩህሩህ አምላኬ የፍቅር ውኃ ምንጭ ኃጢአት እንዳይጥለኝ ያዝከኝ በቸርነት አዝ፦ የሕይወት ውኃ ምንጭ የነፍስ ሁሉ እረኛ ያንቀላፋው ልቤ በውሃው ይነሳል አፍስስ ቅዱስ መንፈስህን ለተጠማች ነፍሴ ይፍለቅ ፍቅርህ ከሕይወቴ ይህ ነው ፀሎቴ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደኔ ይምጣ ብለሃል የሕይወት ውኃ ወንዝ በሰው ሁሉ ላይ ያድራል የመንፈስ አንደበት የሰማያት እንባ ፈሰሰ ከዓይኔ መቼም ላልጠማ አዝ፦ የሕይወት ውኃ ምንጭ የነፍስ ሁሉ እረኛ ያንቀላፋው ልቤ በውሃው ይነሳል (ማንም ለተጠማ የምትሰጥ እርካታ) አፍስስ ቅዱስ መንፈስህን ለተጠማች ነፍሴ ይፍለቅ ፍቅርህ ከሕይወቴ ይህ ነው ፀሎቴ የሕይወት ውኃ ምንጭ በውኃው ይነሳል አፍስስ ቅዱስ መንፈስህን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection