Song Lyrics

ዘመናት አይለውጡህም

Abraham and Eyasu
Zemenat Ayilewituhim
ዘምን በዘመን ሲፈራረቅ ቀኑም ለቀኑ ቦታም ቢለቅ በዓመታት መሃል በቀናት ቁጥር ከፍ ከፍ እያልክ የምትከብር (2x) የጊዜ ኃይል አይለውጥህም አንተ ህያው ነህ አትቀየርም ሚመስልህ የለም የሚገዳደርም ማነው ኃይልህን የሚከለክልህ (2x) አዝ:- ዘመናት አይለውጡህም ዓመታት አይሽሩህም ቀናት አይቀይሩህም አንተ ሁሌ አንተ ነህ ኢየሱስ ነህ አንተ አልፋ ኢየሱስ አንተ ኦሜጋ ኢየሱስ ለዘለዓለም ኢየሱስ የሚመስልህ የለም ቢፈራረቁ ክረምት ከበጋ አንተ ግን ያው ነህ አልፋ ኦሜጋ ጊዜው ሲገሰግስ እንደ ሰረገላ አንተ አታረጅም አትቀርም ኋላ (2x) ሁሉ ፈጥረሃል በስልጣንህ ተከናወነ በይሁን ቃልህ በዙፋንህ ላይ ስንት ነዋሪ አቻ የለህም ተወዳዳሪ ተገዳዳሪ አዝ:- ዘመናት አይለውጡህም አመታት አይሽሩህም ቀናት አይቀይሩህም አንተ ሁሌ አንተ ነህ ኢየሱስ ነህ አንተ አልፋ ኢየሱስ አንተ ኦሜጋ ኢየሱስ ለዘለዓለም ኢየሱስ የሚመስልህ የለም (የሚመስልህ የለም) የጥንቱ ክንድህ ይሰራል ዛሬም ግሩም ችሎታህ አልተቀየረም አንተ አትሻር አትለወጥም ኢየሱስ ህያው ነህ ለዘለዓለም (2x) በሙሴ ዘመን ባህሩን ከፍለህ በሐዋርያት ማዕበሉን ገሰጽክ ብዙ ሰርተሃል በየዘመናት እጅግ ድንቅ ነው የአንተ ተዓምራት አዝ:- ዘመናት አይለውጡህም አመታት አይሽሩህም ቀናት አይቀይሩህም አንተ ሁሌ አንተ ነህ ኢየሱስ ነህ አንተ አልፋ ኢየሱስ አንተ ኦሜጋ ኢየሱስ ለዘለዓለም ኢየሱስ የሚመስልህ የለም (2x) ዘመናት አይለውጡህም አመታት አይሽሩህም ቀናት አይቀይሩህም አንተ ሁሌ አንተ ነህ ኢየሱስ ነህ አንተ አልፋ ኢየሱስ አንተ ኦሜጋ ኢየሱስ ለዘለዓለም ኢየሱስ የሚመስልህ የለም (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection