መድኃኒቴን አየዋለሁ ዓይኖቼ ተከፍተዋል በደሙና በስሙ ስላነጻን ፍፁም ህይወት አሁን አለኝ በሞቱ ፈወሰኝ አሮጌው ልማድ ከሕይወቴ ጠፍቷል አዝ:- አምላኬን ላመስግን ሥሙንም ልወድስ ስላፈቀረኝ በመስቀል ተሰቅሎ (ሃሌሉያ) በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ኢየሱሴን ልወድስ ለዓለም ህዝቦች የፍቅሩን ወንጌል ልግለጽ (2x) ትኩስ ቀዝቃዛ ለብ ያለ ህይወት አትመኑ የጌታ አገልጋይ እሳት ነበልባል ነው በመንፈስ እሳት ግላቹህ እርሱን አገልግሉ የድሉን አክሊል እንድትቀበሉ አዝ:- አምላኬን ላመስግን ሥሙንም ልወድስ ስላፈቀረኝ በመስቀል ተሰቅሎ (ሃሌሉያ) በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ኢየሱሴን ልወድስ ለዓለም ህዝቦች የፍቅሩን ወንጌል ልግለጽ (2x) ነፍሴ አርፋለች በዙፋንህ ሥር በጥላህ እታመናለሁ መፍትሄ የሌለው ምንም ችግር እንደማያገኘኝ አውቃለሁ ከአንተ የተሻለ ጓደኛ የለኝም ከአንተ የቀረበ ዘመድ አላገኝም ከአንተ የበለጠ ምንም አልመኝም ሆሆሆ ኢየሱስ አለልኝ ምንም አይጐለኝም (3x)