Song Lyrics

ዳንኩኝ

ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ሁሉም ነገር አልፏል አሮጌው ማንነት በኢየሱስ ደም ታጥቦ ነፃነት ያገኘ ማን እንደ እኔ ያለ (x2) ዳንኩኝ (x2) ዳንኩኝ እኔ ዳንኩኝ ዳንኩኝ (x2) ዳግም ተወለድኩኝ (x2) ሀጢያት ሚያስጨንቀኝ የእዳ ፅፈቴ ሰላምን የማላውቅ ተቅበዥባዥ ህይወቴ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሞቶልኝ ስለእኔ ህይወትን አገኘው ነፃ ሰው ነኝ ዛሬ ነፃ ከሀጥያት እስራት ነፃ የለብኝም ስጋት ነፃ ሞቴ ተሻረልኝ ነፃ ኢየሱስ ከፈለልኝ (x2) አመሠግናለው በህይወት መዝገብ ላይ አመሠግናለው ስሜን ስለ ፃፍከው አመሠግናለው ለሞት ስላልተውከኝ አመሠግናለው ልጅህ ስላረከኝ አመሠግናለው ብዙ ሆኖልኛል አመሠግናለው መች ይሄ ይገባኛል አመሠግናለው ሌላ ምን እላለዉ አመሠግናለው ህይወቴ ያንተ ነው ዳንኩኝ (x2) ዳንኩኝ እኔ ዳንኩኝ ዳንኩኝ (x2) ዳግም ተወለድኩኝ (x2)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection