Song Lyrics

ናፍቄአለሁ

አንተን ሳላይ እንዲ ከወደድኩህ ካፈቀርኩህ በፍቅርህ ብዛት እንዲህ ከነገርኩህ ያየሁ እለት አንተን ፊት ለፊት እንዴት ልሆን ባላዉቅም ደስታዬ ፍፁም ይሆናል ህይወቴ ፍፁም ይሆናል x4 በላይ በሰማይ በጉ ሠርግ ላይ እኛ ልጆችህ ተሰብስበን ሳይ ሁሉም በደስታ አብሮ ሲዘምር በዚያ አዲስ ሰማይ በተስፋ ምድር ናፍቄአለሁ አዲሱን ቤቴን ናፍቄአለሁ ዘላለም ቤቴን x2 በምድር ያለኝ ህይወት ቢያበቃም ሰማይ ይቀጥላል የሱስ ካንተ ጋር ሞት እንኳን ቢሆን መች ያስፈራኛል ፊትህን እንዳይ ቤትህ ያደርሰኛል ናፍቄአለዉ አዲሱን ቤቴን ናፍቄአለዉ ዘላለም ቤቴን x3 ወደ አንተ እስክሄድ ወይ እስክትመጣ እናፍቃለዉ የነፍሴ ጌታ እስከዚያ ድረስ አንተ ጠብቀኝ የክብር ቤቴ ፅዮን አድርሰኝ ናፍቄአለዉ አዲሱን ቤቴን ናፍቄአለዉ ዘላለም ቤቴን x3
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection