Song Lyrics

አሸንፈናል

በክርስቶስ ኢየሱስ ስራ ነፃ የወጣን ከጨለማው ስራ (x2) የልጅነት ስልጣን ያገኘን ከማይጠፉ የሰማይ ዘር ነን ይህን አለም አሸንፈናል (x2) ከ እግዚአብሔር ነን አሸንፈናል ጨለማዉን አሸንፈናል ይህን አለም አሸንፈናል (x2) ተወልደናል አሸንፈናል ከኢየሱስ ዘር አሸንፈናል ሰራዊቶች ነን የሰማይ ዜጋ መሪያችን የሱስ የሁሉ ጌታ የጠላት ሰፈር ገና ይወረራል ወንጌሉ በኛ ምድርን ይከድናል ይህን አለም አሸንፈናል (x2) ከ እግዚአብሔር ነን አሸንፈናል ጨለማዉን አሸንፈናል ይህን አለም አሸንፈናል (x2) ተወልደናል አሸንፈናል ከኢየሱስ ዘር አሸንፈናል የኪዳን ልጆች ጠላት አይችለን እኛን ሊያጠፋ ብዙ ሞከረን ዘራችን ቅንጣት ገና ይበዛል በእኛ ዉስጥ ያለዉ ካለም ይበልጣል እሳት በኛ ዉስጥ አለ ማይጠፋ ከቶ የማይቆም ገና ሚሰፋ ከጫፍ እስከ ጫፍ የየሱስ ዝና በመንፈስ ቅዱስ ይሰማል ገና እግዚአብሔር ከኛ ጋር አለ ከኛ ጋር (x2) ኢየሱስ ከኛ ጋር አለ ከኛ ጋር (x2) ማነዉ ሚቋቋመን አለ ከኛ ጋር ማነዉ የሚይዘን አለ ከኛ ጋር ማነዉ የሚያቆመን አለ ከኛ ጋር ማነዉ የሚችለን አለ ከኛ ጋር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection